ለተቋሙ ሴት ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
ጥቅምት 14/2017 ዓ.ም
አዳማ
የኢትዮጵያን ፀረ – አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ለሴት ሰራተኞች በአዳማ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እያካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዩ ገዛኸኝ እንደተናገሩት
ጤናማ ዜጋ ለማፍራት እና ጤነኛ ሆኖ ለመቀጠል ስለ ጤና ማወቅ ተገቢ ስለሆነ የሚቀርበውን ስልጠና በጥሞና በመከታተል ጤናችንን የምንጠብቅበትና ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለቤተሰቦቻችን ያገኘነውን እውቀት በማስተላለፍ እና ለመጠቀም ዓላማ ተደርጎ የተዘጋጀ የስልጠና ኘሮግራም ነው ብለዋል።
አክለውም የሴቶች ፎረሙ በተጠናከረ መልኩ እንዲሄድ የ2016 ዓ.ም አፈፃፀም በመገምገምና ለ2017 የምንማርበትን በማዳበር ኑቁ በሆነ መልኩ የሴቶችን ተሳታፊነት በሚያረጋግጥ እና የሴቶችን መብት በሚያስከብር እንዲሁም ግዴታችን የምንወጣበት መልኩ ፎረሙ ና የተቋሙ የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ስራ አስፈፃሚ ተደጋግፈን የምንሄድበት ይሆናል ስለዚህ ይህን ኘሮግራም ትኩረት ሰጥታችሁ እንድትከታተሉ ይገባል ሲሉ ምክትል ዳይሬክተሯ ተናግረዋል ።
ስልጠናው ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን
በዛሬው ዕለት የጡት ካንሰር ና የማህፀን በር ካንሰር በሚመለከት ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ተጋባዥ እንግዳ ዶ/ር አባተ ጋሻሁን /ረዳት ኘሮፌሰር / ስልጠና ተሰቷል። በመቀጠል የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የሴቶች ፎረም እቅድ ዙሪያ በወ/ሮ ወይንሸት ሙሉጌታ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በመርሐግብሩ አጠቃላይ የተቋሙ ሴት ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን ፕሮግራሙ በነገውም ዕለት የሚቀጥል ይሆናል፡፡

By Ermias