ለኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ማህበር አባላት በስፖርት አበረታች ቅመሞች ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም
አዳማ
የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ችግር በዘላቂነት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሰፊ ትኩረት ሰጥቶት በየጊዜው ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት የግንዛቤ ለማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በአዳማ ከተማ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ስፖርት ማህበር ጋር በመቀናጀት ለስፖርት ሳይንስ ምሁራን በስፖርት አበረታች ቅመሞች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰቷል።
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ በመድረኩ ካስተላለፉት መልዕክት አበረታች ቅመሞች በስፖርት እያደረሰ ያለው ጉዳትና በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን ተፅዕኖ ስፖርቱ በአለም አደባባይ የተፈለገው ውጤት እንዳያመጣ የራሱን አስተዋጽኦ እያደረገ ያለ የስፖርቱ ጠንቅ መሆኑን ገልፀው የዩኒቨርስቲ ማህበሩ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር ሥራዎችን በተጠናከረ መልኩ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ክብርት ዳይሬክተሯ አክለውም ትምህርት ሚኒስቴር ከኛ ተቋም ጋር በመሆን ከ5-12 ክፍል በመደበኛ ትምህርት 8 የትምህርት አይነት ውስጥ ተካቶ አበረታች ቅመሞች ምንነትና ጎጂነቱን በትምህርት ደረጃ እንዲሰጥ አድርጓል ብለዋል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በቀጣይ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደረጃ አበረታች ቅመሞች በተመለከተ በትምህርት ውስጥ ተካቶ ሊሰጥ ይገባል የሚል አቋም ይዞ ይህን ከግብ ለማድረስ ከማህበሩ ጋር በተቀናጀ መልኩ መስራት ትልቅ አስተዋፅኦ አለው በማለት ክብርት ዳይሬክተሯ መልእክታቸውን አስተላልፏል ።
በዋናነት ስልጠናው የፀረ-አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴ በአለም አቀፍና በኢትዮጵያ ፣ የአበረታች ቅመሞች ፅንሰ ሃሳብ፣ የተከለከሉ ንጥረ ነገሮች እና ዜዴዎችና የሚያስከትሉ ጉዳት፣ በአሰራር ስርአቶች እና ባሉት ሕግና ደንቦች በአበረታች ቅመሞች መከላከል ግንዛቤ እና ህዝብ ንቅናቄ መሪ ሥራ አስፈፃሚ በአቶ ፈለቀ ዋለልኝ እና ከፍተኛ የስልጠና ባለሙያ በወ/ሮ ወይንሸት ሙሉጌታ ለተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ገለጻ አድርጓል ።

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *