በሀዋሳ ከተማ ንፁህ ስፖርት ለጤናማ ዜጋ በሚል መሪ ቃል የፀረ-ዶፒንግ የቅስቀሳና የህዝብ ንቅናቄ ፕሮግራም በተለያዩ ሁነቶች ተካሄደ።
ነሐሴ 27/2ዐ16 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ፀረ – አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሀዋሳ ከተማ ከነሐሴ 24 -25 ዓ.ም የተለያዩ ፕሮግራሞች በማዘጋጀት ሰፊ የህዝብ ንቅናቄ ስራዎች መስራት ችሏል።
በከተማው ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በጋራ በመሆን የፀረ – አበረታች ቅመሞች የፖናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ ላይ ከሀዋሳ ዪኒቨርስቲ መምህራን፣ ታዋቂ አትሌቶች ፣ ለአትሌት ማናጀሮች እና አስልጣኞች፣ ከክልሉ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ጉዳዮ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ፖናል ውይይት አካሄዷል።
እንዲሁም የፀረ-አበረታች ቅመሞች የህዝብ ንቅናቄ የ (Social Campaign) በስምንቱም ክፍለ ከተማ በተሽከርካሪ በመዘዋወር የፀረ – ዶፒንግ የቅስቅሳ መልዕክቶች በማስተላለፍ እና ማህበረሰብ አቀፍ የአውትሪቺንግ ፕሮግራም በማካሄድ የማህበረሰቡ ግንዛቤ በማሳደግ እና ሰፊ የህዝብ ቅስቀሳና ንቅናቄ ስራዎችን በመስራት ማህበረሰቡን በዶፒንግ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው ተችሏል ።
ፕሮግራሙም አዝናኝ በሆነ መልኩ በስፖርት አበረታች ቅመሞች መሰረታዊ ሃሳብና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ግንዛቤ እንዲጨብጡ የሚያስችሉ ጥያቄና መልስ ውድድር እና የተለያዩ የህትመት ውጤቶች ብሮሽሮች ፣ቲሸርቶች ለታዳሚዎች የተሰራጨ ሲሆን እንዲሁም አስተማሪ መልዕክት የያዙ ባነሮች ተዘጋጅተው በስፍራዎች በመስቀል እና የፀረ-ዶፒንግ መልዕክቶች በማይክ እንዲተላለፍ ተደርጓል፡፡