ታዳጊ ወጣቶች ከስፖርት ስልጠና ጎን ለጎን ስለስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ መሰረታዊ ጉዳዮች ግንዛቤ ሊጨብጡ እንደሚገባ ተጠቆመ፤ ለጥሩነሽ ዲባባ የአትሌቲክስ ማሰ ማልጠኛ ማዕከል ስፖርተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ቀን ግንቦት 21/2010 ዓ.ም

የአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል በተለያዩ ስፖርቶች በተለይም በአትሌቲክስ ተተኪ ስፖርተኞችን በማፍራት የአገራችንን ውጤታማነት ለማጎልበት ተቋቁሞ ታዳጊ ወጣት ስፖርተኞችን በማሰልጠን ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ከዚህም ጋር ተያይዞ የወደፊት የአገራችን ስፖርት ተተኪ የሆኑ ወጣት አትሌቶች ከስፖርታዊ ስልጠናው ጎን ለጎን በስፖርት አበረታች ቅመሞች/ዶፒንግ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ማድረግ ተገቢ በመሆኑ ለማዕከሉ አትሌቶች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በስልጠናው ላይም አትሌቶች በቀጣይ የማዕከሉን ስልጠና አጠናቅቀው ወደ ተለያዩ ክለቦችና የአገራችን ብሄራዊ ቡድኖች ውስጥ ተቀላቅለው በአለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ውስጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመሳተፍ ራሳቸውን ከስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ መጠበቅ እንዳለባቸው የተጠቆመ ሲሆን በስፖርት አበረታች ቅመሞች ምንነትና በሚያስከትላቸው የጎንዮሽ ጉዳቶች፣ በድጋፍ ሰጪ ምግቦች (Supplements/Vitamins)፣ በተለያዩ የስፖርት አበረታች ቅመሞች ህጎች፣ በየደረጃው በስፖርተኞች የህክምና አሰጣጥ እና በተለያዩ ርዕሰ-ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *