በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ስር ለሚገኙ ሰልጣኞች ፣ አሰልጣኞች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ፀረ- ዶፒንግ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ።
ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ጋር በመቀናጀት በአካዳሚው ለሚገኙት ሰልጣኞች ፣ አሰልጣኞችና ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ፀረ ዶፒንግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
ከኢትዮጵያ የስፖርት አካዳሚ ትምህርት ስልጠናና ውድድር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ በላይ በስልጠና መድረክ በመገኘት ካስተላለፉት መልዕክት አበረታች ቅመሞች አትሌቶች ትልቁን ህልማቸውን የሚያጨናግፍ እና ከአላማና ከግብ ውጪ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል ።
አክለውም እንደተናገሩት በዚሁ ጉዳይ ከስፖርቱ ውጪ የሆኑ አትሌቶች ህይወታቸው የተስተጓጐሉ ስመ ጥር ይሆናሉ ተብለው የታሰቡት አትሌቶች በቀላሉ ተጨናግፏል በማለት ገልፀው በአካዳሚው የሚገኙ አትሌቶች ከአበረታች ቅመሞች እራሳቸውን መጠበቅ እንደሚገባ ገልፀው ይህ ስልጠና የህይወታችሁ ትልቅ የግብ ስኬት የሚወስንበት ነው በማለት መልእታቸውን አስተላልፏል።
ስልጠናው ከኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የአበረታች ቅመሞች መከላከል ግንዛቤ እና ህዝብ ንቅናቄ ሥራ አስፈፃሚ ከፍተኛ ባለሞያዎች አቶ ሰይፉ በላይነህ እና ወ/ሮ ወይንሸት ሙሉጌታ በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦች ፣ የተከለከሉ ንጥረ ነገሮች እና ዜዴዎች ፣ በአሰራር ስርአቶች፣ የሚያስከትለውን ጉዳት እና ባሉት ሕግና ደንቦች እንዲሁም በምርምር እና ቁጥጥር ሂደት ዙሪያ ለሰልጣኞች ሰፋ ያለ ገለጻ እና ማብራሪያ አድርጓል።

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *