በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስፖርት አበረታች ቅመሞች ዙሪያ የግንዛቤና ንቅናቄ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት ተጠናቀቀ።
ህዳር 18/2017 ዓ.ም
ቦዲቲ
የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጋር በመተባበር በአበረታች ቅመሞች ዙሪያ የግንዛቤና ንቅናቄ ፕሮግራም በማካሄድ ላይ መሆኑ ይታወቃል በዚህ መሠረት በዛሬው ዕለትም በወላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ ለሚገኙ የቴኳንዶ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች፣የእግር ኳስ ፕሮጀክቶችና አትሌቶች ቦዲቲ ወጣቶች መዝናኛ ማዕከል ግንዛቤ እንዲፈጠር በማድረግ የስልጠናው መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።
የዶፒንግን መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦች ፣ የተከለከሉ ንጥረ ነገሮች እና ዜዴዎች ፣ የሚያስከትለውን ጉዳት እና ባሉት ሕግና ደንቦች እንዲሁም በምርምር እና ቁጥጥር ሂደት ዙሪያ ያተኮረ ነበር።

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *