የስፖርቱን ማህበረሰብ ግንዛቤ ለማሳደግና ንቅናቄ ለመፍጠር በሱሉልታ ከተማ የስፖርት አበረታች ቅመሞች /የፀረ -ዶፒንግ/ (አውትሪቺንግ ) ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል።
ህዳር 27/ 2017 ዓ.ም
ሱሉልታ
የኢትዮጵያ ፀረ -አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ኦሮሚያ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት ከህዳር 27_29/2017 ዓ.ም በሱሉልታ ከተማ በሚካሄደው 1ኛ ዙር የኦሮሚያ የስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላት ውድድር ላይ እየተሳተፉ ለሚገኙ አትሌቶች፣ የአትሌት ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ግንዛቤ ለማሳደግና ንቅናቄ ለመፍጠር የፀረ-ዶፒንግ የOutreaching ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሙ የአትሌቶችን፣ የስፖርት ባለሞያዎች ፣ የሰፖርት አመራሮችንና የስፖርቱን ማህበረሰብ ግንዛቤ በማሳደግ እና ሰፊ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር ከዶፒንግ ነፃ የሆኑ ስፖርተኞችን ለማፍራት የተዘጋጀ መርኃ ግብር ነው ፡፡
ፕሮግራሙም አዝናኝ በሆነ መልኩ በስፖርት አበረታች ቅመሞች መሰረታዊ ሃሳብና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ግንዛቤ እንዲጨብጡ የሚያስችሉ ጥያቄና መልስ ውድድር ፣ ጨዋታዎች እና የተለያዮ ፕሮሞሽናል ማቴሪያል (ብሮሸሮቸ ፣ቲሸርቶች ) ለታዳሚዎች እየተሰራጨ ይገኛል ፡፡




