የአለም አትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት (AIU) የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣንን በዛሬው እለት ጉብኝት አደረገ።
መስከረም 15/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአለም አትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት (AIU) አውቶ ኮምፒቴሽን ቴስት ማኔጀር አቶ ራፋያል ሮክስ የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የስራ ኃላፊዎች ጋር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ በዛሬው እለት በተቋሙ ተገኝተው ውይይት አካሄዷል።
በውይይቱም ወቅት የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን አጠቃላይ እንቅስቃሴና እየተሠሩ ስላሉ ሥራዎች በአቶ መንግስቱ የምሩ ገለፃ ተደርጓል፡፡
የአለም አትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት (AIU) አውቶ ኮምፒቴሽን ቴስት ማኔጀር አቶ ራፋያል ሮክስ ሀገራችን አበረታች ቅመሞችን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ እያከናወነች ያለው ተግባር የሚበረታታ እንደሆነ በውይይቱ ወቅት ገልፀው በቀጣይ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።