የአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ምርመራ ሂደቱን (Testing Procedures) ሙሉ ለሙሉ ዲጂታላይዝ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት ሥራው  ተጠናቋል።

ጥቅምት  6/2017 ዓ.ም

አዳማ

የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ንጹህ ስፖርትን ለማስፋፋትና ጤናማ የሆኑ ስፖርተኞችን ለማፍራት የአትሌቶችን ግንዛቤ ከማሳደግ ባለፈ የስፖርት አበረታች ቅመሞች ምርመራና ቁጥጥር ስራን በተጠናከረ መልኩ  እየሰራ ይገኛል፡፡

በዚህም  የምርመራ ሂደቱን (Testing Procedures) ሙሉ ለሙሉ ዲጂታላይዝ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶት በመሰራት ላይ የሚገኝ ሲሆን  ለአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ የምርመራ ባለሙያዎች (Sample Collection Personnel)  በተለያዪ ርዕሰ ጉዳዩች በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተደገፈ ሙያዊ ስልጠና ተሰጠ ፡፡

ስልጠናው ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ  የቆየው ሲሆን የባለሞያዎቹም አቅም በማሳደግና ብቃት ያላቸው ሙያተኞችን በማፍራት የምርመራ ሂደቱንም ሙሉ ለሙሉ ዲጅታላይዝ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት ሥራው ተጠናቋል።

 

By Ermias