የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የበላይ አመራር ከ ክልል ከተማ የስፖርት ዘርፍ የበላይ አመራሮች ጋር ሲያደርግ የነበረውን ውይይት አጠናቀቀ ።
ሰኔ 11/2016 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የበላይ አመራር ከሐረሪ ብሄራዊ ክልል፣ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና ከሱማሌ ብሄራዊ ክልል የስፖርት ዘርፍ የበላይ አመራሮች ጋር በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ መከላከልና መቆጣጠር እንቅስቃሴ ዙሪያ ውጤታማ ውይይቶችን በማካሄድ ቆይታውን አጠናቋል ።
ልኡክ ቡዱኑ ከላይ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይቶች በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና በሐረሪ ክልል ጅምር የሆኑ የፀረ-አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴዎች በተለይም የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች በመካሄድ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ይህ እንቅስቃሴ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚጠበቅባቸው ከአመራሮቹ ጋር የጋራ መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን በተለይም ራሱን የቻለ መዋቅር መክፈትና የሰው ኃይል ማሟላት፣ የግንዛቤ ማስጨበጥና የህዝብ ንቅናቄ፣ በየደረጃው ክትትልና ቁጥጥር እና የመሳሰሉት ተግባራት ከስፖርቱ ልማት ጎን ለጎን በቂ ትኩረት ተሰጥቷቸው መከናወን እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡
በሌላም በኩል የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን መሰል ውይይቶችን ከሌሎች የክልል አስተዳደር ስፖርት ዘርፍ አመራሮች ጋር እያደረግ ሲሆን በቀጣይ ይህን እንቅስቃሴ በማጠናከር ቅንጅታዊ አስራሮቹን በመዘርጋት በክልሎች ያለውን ተደራሽነት በይበልጥ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም ለስፖርተኞች እና ለስፖርት ባለሞያዎችም በፀረ አበረቻች ቅመሞች /ዶፒንግ / የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።