የፀረ-ዶፒንግ የOutreaching ፕሮግራም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተካሄደ ፡፡
ሰኔ 28/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ባዘጋጀው የክረምት በጉ ፈቃድ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ፕሮግራም ላይ ለሚሳተፉ በጉ ፍቃደኞች እና ስፖርተኞች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ግንዛቤ ለማሳደግና ንቅናቄ ለመፍጠር የፀረ-ዶፒንግ የOutreaching ፕሮግራም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም አካሄደ፡፡
በግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሙ ላይ ከሁሉም ክፍለ ከተማ የተወጣጡ በጉ ፈቃደኞች እና ስፖርተኞች የተሳተፉ ሲሆን ይህም በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና ጤናማ ስፖርተኞች እንዲኖሩ የሚያስችል ነው፡፡
በዚህ ፕሮግራም ላይ በስፖርት አበረታች ቅመሞች መሰረታዊ ጽንሰ ሃሳብና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ግንዛቤ እንዲጨብጡ የሚያስችል ጥያቄና መልስ ውድድር ፣ የተለያዩ የህትመት ውጤቶች ብሮሽሮችና ቲሸርቶች የተስራጩ ሲሆን እንዲሁም አስተማሪ መልዕክት ያዘሉ ባነሮች ተዘጋጅተው በውድድር ስፍራዎች ተሰቅለዋል።