ለኢትዮ-ኤሌትሪክ አትሌቲክስ ብድን ስልጠና ተሰጠ::
የካቲት11/2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን/ETH-ADA/ ለኢትዮ-ኤሌትሪክ አትሌቲክስ ቡድን በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒነግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በአዲሰ አበባ፣አራራት ሆቴል ተሰጥቷል፡፡
በመድኩ ላይ 85 የሚሆኑ አትሌቶች፤ የአትሌት ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን በዶፒንግ ምንነት፤በሚያስከትለው ጉዳት፤የህግ ጥሰት፤ምርመራ ሂደትና በተዘረጉ ያሰራር ሥርዓቶችና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የኢትዮ-ኤሌትሪክ አትሌቲክ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አቶ መላኩ ደረሰ እዳሉት ከስፖርቱ ስልጠና ጎን ለጎን የዶፒንግን መሰረታዊ ጉዳዮች አውቆ ወደተግባር መቀየር ከእያዳንዱ አትሌት ሆነ ባለሞያው የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን ገልጸው፤ ስልጠናውን በትኩረት እዲከታተሉ በማሳስብ መድረኩን አስጀምረዋል ፡፡
ትምህርቱን የተሰጠው የባለሥልጣኑ የትምህርትና ስልጠና ባለሞያዎች በሆኑት በአቶ ዳንኤል ተስፋዬና በአቶ ሐብታሙ ካሱ ነው፡፡
መድረኩ የተዘጋጀው ከኢትዮ-ኤሌትሪክ አትሌቲክስ ቡድን ጋር በመተባበር ነው፡፡