አትሌት ብርሃኑ ፀጉ የተከለከለ የስፖርት አበረታች ቅመም ወይም ዶፒንግ መጠቀሙ በመረጋገጡ ለ4(አራት) ዓመታት በማንኛውም ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ እገዳ ተጥሎበታል፡፡
አትሌት ብርኃኑ ፀጉ ቀደም ሲል እ.ኤ.አ መስከረም 15/2019 ዴንማርክ ኮፐንኃገን በተካሄደው የግማሽ ማራቶን የግል ውድድር ላይ የተከለከለ የስፖርት አበረታች ቅመም ወይም ዶፒንግ በመጠቀም ተጠርጥሮ ላለፉት 7(ሰባት) ወራት ጉዳዩ ሲጣራ ቆይቷል፡፡
ስለሆነም በተደረገው ተጨማሪ ኢንቨስቴጌሽንና የማጣራት ተግባር አትሌቱ በግሉ በተሳተፈበት ውድድር ላይ Erythropoietin (EPO) የተባለውን በስፖርት የተከለከለ አበረታች መድኃኒት መጠቀሙ ተረጋግጧል፡፡ ለዚህም አትሌቱ የፈፀመው ጥፋት የመጀመሪያ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት እ.ኤ.አ ከመስከረም 15/2019 ጀምሮ እስከ መስከረም 14/2023 ድረስ ለ4 (አራት) ዓመታት በማንኛው አገር አቀፍም ይሁን አለም አቀፍ ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ እገዳ ተጥሎበታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዚህ ውድድር ላይ ብቻ ያስመዘገበው ውጤት እና ሽልማት እንዲሰረዝ ውሳኔ ተላልፏል፡፡
እ.ኤ.አ በ2019 በአጠቃላይ 3(ሶስት) አትሌቶች በተለያዩ አለም አቀፍ ውድድሮች በግላቸው ባደረጓቸው ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን መጠቀማቸው በመጠርጠሩ ጉዳያቸው በመጣራት ላይ ሲሆን ውሳኔ እንደተጠናቀቀ ቅጣቱንና ስም ዝርዝራቸውንም የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
በዚሁ አጋጣሚ በአገራችን በየደረጃው የሚደረገው ምርመራና ቁጥጥር ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት የስፖርት አበረታች ቅመሞችን በመጠቀምም ይሁን በተለያዩ መልኩ የፀረ-ዶፒንግ የህግ ጥሰት በሚፈፅሙ አትሌቶችና ከጀርባ ሆነው ተሳታፊ በሚሆኑ ሌሎችም ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን የእርምት እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ይገልፃል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት
የEth Nado ምስል
የEth Nado ምስል

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *