የኢፌድሪ ስፖርት ኮሚሸን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ- አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት እና ከኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ጋር በመተባባር ለስፖርት ጋዜጠኞች ባያዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ -አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ውይይት አካሄደ::
አዳማ ፣ የካቲት 05/2013 የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ የኢፌድሪ ስፖርት ኮሚሽ ፣ የኢትዮጲያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር እና የስፖርት ጋዜጠኞች በተገኙበት ጋር ውይይት አደረገ ::
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ም/ዋና ዳሬክተር ወ/ሮ ፋንታዪ ገዛህኝ ስነዱን ያቀረቡ ሲሆን የ10 ዓመት እቅዱ እስከ 2022 ዓ.ም ለማከናወን የታቀደ በመሆኑ የፖሊሲና ስትራቴጂ ፣ ያለፉትን የሶስት አመታት የጽ/ቤቱ የስራ አፈጻጸም ፣ ዓለም አቀፍና አገራዊ ሁኔታዎችን እንዲሁም ግቦችን መሠረት በማድረግ ቴክኒካል ኮሚቴዎችን በማዋቀር የታቀደ ነው ብለዋል ።
የነበሩ ጥንካሬዎችን ፣ ድክመቶችን ፣ ስጋቶችንና መልካም አጋጣሚዎችን ያካተተው ይህ እቅድ የቴክኒካል ኮሚቴዎችን ፣ አመራሮችን ፣ ቋሚ ሰራተኞችን እንዲሁም የባለድርሻ አካላትን እቅዱን ለመተግበር አጠናክሮ እንደሚሄድ በእቅዱ ተመላክቷል።
እቅዱ በ7 ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ያሉት ሲሆን የትምህርትና ስልጠና፤ የህዝብ ንቅናቄ ማሳደግ የምርመራና ቁጥጥር አሰራሮችን አጠናክሮ ማስቀጠል ፤ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን፤ የቁጥጥርና የክትትል በየእርከኑ አጠናክሮ ማስቀጠል ፤አለም ዓቀፍ ግኑኝነት የማጎልበት ስራዎች ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማከናወን መታቀዱ ዳሬክተሯ ገልጸዋል፡፡
በዚህም በሚቀጥሉት አስር ዓመታት በመሪ እቅዱ ይተገበራሉ ተብለው ከተያዙት ውስጥ የጸረ -ዶፒንግ ጽንሰ ሀሳብ በትምህርት ካሪኩለም ላይ ማካተት ፣ በክልልና በፌደራል ደረጃ በስፖርት ስልጠና ማዕከላት ላይ የዶፒንግን ሀሳብ በስልጠና ማኗል ላይ አያይዞ መስጠት እንዲሁም በአለም አቀፍ ስታንዳርድ መሰረት ደረጃውን የጠበቀ ላብራቶሪ በአገራችን መገንባት እና ዝርዝር ጉዳዮች በእቅዱ ትኩረት የተሰጣቸው መሆናቸውም ተናግረዋል::
በመጨረሻ ከመድረኩ ለተነሳው ጥያቄ የጽ/ቤቱ አመራሮች ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መኮንን ይደርሳልና ም/ ዋና ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ፋንታዪ ገዛህኝ ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡
+3
<img class="j1lvzwm4" src="data:;base64, ” width=”18″ height=”18″ />
Erim Beza Chegen, Ahmed Nejat and 17 others
2 Shares
Like

Comment
Share

Comments

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *