የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጸ/ቤት /ETH-NADO/ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ7ኛ በጊዜ በአገራችን ደሞ ለመጀመሪ ጊዜ የዓለም አቀፍ የፀረ- ዶፒንግ ቀንን ‹ከዶፒንግ ነጻ ቀን፤ እራሳችንን ከኮሮና እንጠብቅ› በሚል መሪ ቃል በፓናል ውይይት ተከበረ፡፡
ሐሙስ መስከረም 21/2013 ዓ.ም
 አዲስ አበባ፤ ሐርመኒ ሆቴል
የፓናል ውይይቱ መስከረም 21/2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሐርመኒ ሆቴል የኤፌድሪ ስፖርት ኮሚሽን፤ባለድረሻ አካላት፤የተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ፤ የጽ/ቤቱ ማናጅመትና ሰራተኞች በተገኙበት በዚህ የፓናል ውይይት ላይ ተገኝተው ፕሮግራሙን ያስጀመሩት የጽ/ ቤቱ ቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር አክሊሉ አዛዥ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በዓሉ ህዝባዊ የፀረ -ዶፒንግ ንቅናቄ ማካሄድ የስፖርቱ ማህበረስብ ባጠቃላይ ህዝቡ በዶፒንግ ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ ለማጎል፤በትና ሰፊ የህዝብ ንቅናቄ ለመፍተር ከፍተኛ እገዛ እዳለው ገልጸዋል፡፡
በመቀጠል ንግግር ያደረጉት የኢፌድሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኢሊያስ ሽኩር በዓሉ በአገር አቀፍ ደረጃ ዶፒንግን በዘላቂነት በመከላከል ንፁህ ስፖርትን ለማስፋፋት ከፍተኛ እገዛ አለው ያሉት ኮሚሽነር ኢሊያስ ሽኩር በዚህ ረገድ ባለድረሻ አካላት በትብብር ሊሰሩ እደሚገባል አስገንዝበዋል፡፡
የጽ/ቤቱ ም/ዋና ዳሬክተር ወ/ሮ ፋንታዪ ገዛኽኝ የጽ/ቤቱን የ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅደ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እደተናገሩት ጽ/ቤታቸው ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣተር ረገድ በአጭር ጊዜ አበረታች ውጤቶች ማስመዝገብ ተችሏል፡፡የተጀመረው እንቅስቃሴ የበለጠ በማጠናከርና ባለድረሻ አካላት ጋር ተቀናጅተው በመስራት ተደራሽነቱን ለማስፋት ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ የበዓሉ ዓላማና የዶፒንግ ታሪካዊ ዳራ በወ/ሮ መሰረት ተሾመ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት መምህርት ቀረርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በዓሉ በተለያዩ ህዝባዊ ንቅናቄ በባነር በተሰቀሉ መልክቶች፤ በዋናዋና የከተማዋ አደባባዮች በተሸከርካሪ መልክቶችን በማስነገር፤ ፌስ ማስክ በማደል እና የህትመት ውጤቶችን በማስራጨት ለሁለት ተከታታይ ቀናት ይከበራል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *