የጽ/ቤቱ የ6 ወር የሥራ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄደ
ቀን፤ አርብ የካቲት12/2013 ዓ.ም አዳማ ከተማ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት /ETH-NADO/ በ2013 የመጀመሪያው ግማሽ በጀት ዓመት ባከናወኗቸው ተግባራት ላይ የጽ/ቤቱ ዳይሬክተሬቶችና ሰራተራተኞች ባሉበት ውይይትና ግምገማ ተካሄደ ፡፡
ከየካቲት 12-13 ቀን 2013 ዓ.ም የሚቆየው በዚህ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ክብር አቶ መኮነን ይደርሳል እና የጽ/ቤቱ የቦርድ አባልና የኢፌድሪ ሰፖርት ኮሚሽን የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን አልዩ ተግኝተዋል ፡፡
መድረኩ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሁን በዛሬ ዕለት የጽ/ቤቱ መጀመሪያው ግማሽ በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጻም ሪፖርት በአቶ ፍቅሩ ንጉሴ የጽ/ቤቱ የእቅድ ዝግጅትና ግምገማ ዳ/ ዳይሬክተር ቀርቧል፡፡
ከምሳ በኃላ የ6 ወር ሥራ አፈጻጸም ላይ ውይይት የተደርገ ሲሆን፡፡ መድረኩን ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መኮንን ይደርሳልና አቶ ሰለሞን አልዩ መርተዉታል፡፡ ከመድረኩ በተነሱት ጥያቄዎች ላይም ሁለቱ አመራሮች ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡
በነገው ዕለት የቀጣይ የበጀት አመቱ የተከለሰ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *