በስፖርቱ ውስጥ በየደረጃው ለሚያገለግሉ ባለሞያዎች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
Read Time:36 Second
ታህሳስ 17/2011 ዓ.ም
በአገራችን በርካታ ባለሞያዎች በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ሰልጥነው በአሰልጣኝነት፣ በዳኝነት፣ በኢንስትራክተርነት እና በመሳሰሉት ዘርፎች በማገልገል ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም እነዚህ የስፖርት ባለሞያዎች በአገር አቀፍ ደረጃ አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣጠር ንፁህ ስፖርትን በማስፋፋት ረገድ ሰፊ ሚና እንደሚጫወቱ ይታመናል፡፡
በመሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት ከፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ ከሁሉም ክልሎች/የከተማ አስተዳደሮች ለተወጣጡ እና ከላይ እንደተገለፀው በ19 የስፖርት አይነቶች በአሰልጣኝነት፣ በዳኝነት እና በኢንስትራክተርነት ለሚያገለግሉ 610 የስፖርት ባለሞያዎች በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ መሰረታዊ ጉዳዮች፣ በየደረጃው በተዘረጉ የአሰራር ስርዓቶችና አደረጃጀቶች፤ በህግ ማዕቀፎች እና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በአዳማ ከተማ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ይህ ስልጠና በቀጣይም ተጠንክሮ የሚቀጥል ሲሆን በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላትን ተደራሽ ለማድረግ እና ሰፊ የህዝብ ንቅናቄ ለመፍጠር ፅ/ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ ይሆናል፡፡
Related Post
The Ethiopian National Anti-Doping Office (ETH-NADO)has provided Anti-Doping awareness
ለኢትዮጲያ ፓራሊምፒክ ኮሚቴ አትሌቶችና አሰልጣኞች በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ፡፡ ቀን፡- አርብ ታህሳስ 9/04/2013 ዓ.ም...
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት በተለያዩ አለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ለሚሳተፉ አትሌቶች የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም የዶፒንግ ምርመራ በዛሬው እለት አካሄደ ፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት በተለያዩ አለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ለሚሳተፉ አትሌቶች የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም የዶፒንግ ምርመራ በዛሬው እለት...
የ6ኛ ቀን የዶፒንግ ግንዛቤ ማሰጨበጫ ሥልጠና መርኃ-ግብር
የ6ኛ ቀን የዶፒንግ ግንዛቤ ማሰጨበጫ ሥልጠና መርኃ-ግብር ለአዳማና ዳዲቦሩ አትሌቲክሰ ክለብ አባላት በዶፒንግ ፅን-ሃሳብ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጠ፡፡ (ETH-NADO...
የ5ኛ ቀን የሥልጠና መርኃ-ግብር
የ5ኛ ቀን የሥልጠና መርኃ-ግብር የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግ የሚመለከቱ ጉዳዮች በክለቡ መደበኛ ስልጠና ካሪኩለም ውስጥ እንዲካተትና ተግባራዊ ለማድረግ እየስራ...
ለማሰልጠኛ ተቋማት በዶፒንግ ላይ የሚሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እደቀጠለ ነው ፡፡
ለማሰልጠኛ ተቋማት በዶፒንግ ላይ የሚሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እደቀጠለ ነው ፡፡ የዛሬው የ4ኛ ቀን ፕሮግራም ለጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት ማስልጠኛ ማዕከል...
የ3ኛ ቀን የስልጠና ፕሮግራም
የ3ኛ ቀን የስልጠና ፕሮግራም ለጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት ማስልጠኛ ማዕከል አትሌቶች በዶፒንግና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው፡፡...
Average Rating