የስፖርቱን ማህበረሰብ ግንዛቤ ለማሳደግና ንቅናቄ ለመፍጠር በአበበ ቢቂላ ስቴድየም የስፖርት አበረታች ቅመሞች /የፀረ -ዶፒንግ /(አውትሪቺንግ ) ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል።
ነሐሴ 12/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ፀረ -አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመቀናጀት በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የሴካፋ የሴቶች ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ተሳታፊ ስፖርተኞች፣ ለስፖርት ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች እና የስፖርቱን ማህበረሰብ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ግንዛቤ ለማሳደግና ንቅናቄ ለመፍጠር የፀረ-ዶፒንግ የOutreaching ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የግንዛቤ ማሳደጊያና ንቅናቄ ፕሮግራሙ የስፖርት ማህበረሰቡ በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው እና ጤናማ ስፖርተኞች እንዲፈጠሩ ለማስቻል ነው፡፡
ፕሮግራሙም አዝናኝ በሆነ መልኩ በስፖርት አበረታች ቅመሞች መሰረታዊ ሃሳብና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ግንዛቤ እንዲጨብጡ የሚያስችሉ ጥያቄና መልስ ውድድር እና የተለያዩ የህትመት ውጤቶች ብሮሽሮች ፣ቲሸርቶች ለታዳሚዎች የተሰራጨ ሲሆን እንዲሁም አስተማሪ መልዕክት የያዙ ባነሮች ተዘጋጅተው በውድድር ስፍራዎች በመስቀል እና የፀረ-ዶፒንግ መልዕክቶች በማይክ እየተላለፈ ይገኛል ፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *