የፀረ-አበረታች ቅመሞች/ፀረ-ዶፒንግ/ የቅስቀሳና ህዝብ ንቅናቄ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው ።

ነሐሴ 24/2016 ዓ.ም
ሀዋሳ

የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ከነሐሴ 24 -25 ዓ.ም የሚቆይ የፀረ-አበረታች ቅመሞች የህዝብ ንቅናቄ የ (Social Campaign) ፕሮግራም እንዲሁም የስፖርት ማህበረሰብ የአውትሪቺንግ ኘሮግራም እያካሄደ ይገኛል።

የፀረ-ዶፒንግ የህዝብ ንቅናቄ የ (Social Campaign) ፕሮግራም እንዲሁም የስፖርቱን ማህበረሰብ የአውትሪቺንግ ኘሮግራም በዛሬው ዕለት ሀዋሳ ከተማ በተሽከርካሪ በመዘዋወር የፀረ – ዶፒንግ የቅስቅሳ መልዕክቶች በማስተላለፍ እና በከተማው በተመረጡ ቦታዎች ላይ ድንኳን በመትከል የፀረ-ዶፒንግ የህዝብ ንቅናቄ ሥራዎችን በሰፊው እየተሰራ ይገኛል ፡፡

በኘሮግራሙ ላይ በዶፒንግ ዙሪያ የተዘጋጁ ብሮሸሮችን በማሰራጨት እና የተለያዩ መልዕክት የያዙ ባነሮች የተዘጋጁ ሲሆን አስተማሪ የሆኑ መልዕክቶችን በማይክራፎን ለህብረተሰቡ እንዲተላለፍ በማድረግ እና ተመልካቾችን ጥያቄና መልስ ውድድር በማሳተፍ ሰፊ የሆነ የስፖርት አበረታች ቅመሞች/ፀረ-ዶፒንግ/ ዙሪያ ግንዛቤና ንቅናቄ መፍጠር ተችሏል ።