የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን አጠቃላይ ሰራተኛው በተገኙበት የጋራ የውይይት መድረክ በማካሄድ ይገኛል ፡፡

ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም
አዳማ

የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች  ባለስልጣን የተቋሙ የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት እቅድ ክንውን፣ የቀጣይ በጀት አመት እቅድ ዝግጅትና የአቅም ግንባታ ስልጠና በአዳማ ከተማ ከነሐሴ 30- ጳጉሜ 1/2016 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የሚቆይ መድረክ  በዛሬው ዕለት የተቋሙ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት  ውይይት እያካሄደ ይገኛል ፡፡

በመድረኩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል እንደተናገሩት
በ2016 ዓ.ም በተቋማችን ስኬታማ የሆኑ አፈጻጸሞች ማስመዝገብ የቻልናባቸው ሁኔታዎች የነበሩበት አመት እንደነበር ጠቁመዋል ፡፡
አቶ መኮንን አክለውም ግምገማው በ2016 በጀት ዓመት ያገኘናቸውን ስኬቶች የምናልቅበትና የምናስፋፋበት እንዲሁም በ2017 ጉድለቶቻችንን በመሙላት እና በማረም ለቀጣይ ዕቅዳችን ጥሩ አቅም የምንፈጥርበት የውይይት መድረክ ሊሆን ይገባል በማለት  ዳይሬክተሩ  አሳስበዋል ።
በተቁሙ የሚሰሩ ስራዎችን ሁሌም በአለም አቀፍ ህጎችና የአሰራር ስርዓቶች መሰረት ባደረጉ መልኩ መከናወን ይኖርባቸውል  በማለት አቶ መኮንን ገልፀዋል  ።

በመቀጠል የተቋሙ የ2016 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጻም ሪፖርት እና የ2017 ዓ.ም እቅድ በወ/ሮ ስርጉት በየነ የስትራቴጂ ጉዳዪች ስራ አስፈጻሚ እንዲሁም የ2017 ዓ.ም እቅድ  ቀርቧል፡፡
በቀረበው ሪፖርት እና እቅድ ከሰራተኛው ጥያቄ ና አስተያየት ቀርቦ በበላይ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰቶበታል የቀጣይ በጀት ዓመት  የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።