በፀረ – አበረታች ቅመሞች ዙሪያ የፖናል ውይይት ተካሄደ ፡፡

ነሐሴ 24/2016 ዓ.ም
ሀዋሳ

የኢትዮጵያ ፀረ – አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሀዋሳ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በጋራ በመሆን የፀረ – አበረታች ቅመሞች የፖናል ውይይት ተካሄዷል ፡፡

በመድረኩ ላይ ከሀዋሳ ዪኒቨርስቲ መምህራን፣ ታዋቂ አትሌቶች ፣ ለአትሌት ማናጀሮች እና አስልጣኞች፣ ከክልሉ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ጉዳዮ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፀረ – አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል ባስተላለፉት መልዕክት፡-
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ስፖርት ኮሚሽን የሥራ ሀላፊዎች፣ ሙያተኞች ይህን ፕሮግራም በደመቀ ሁኔታ ሰፋ ባለ ፓኬጅ በምንወዳት ሁሌም በምንናፍቃት ከተማ በሀዋሳ እንድናዘጋጅ ላስተባበሩልና ከፍተኛ የሆነ እገዛ እያደረጉልን ስላሉ በጣም እጅግ አድርገን እናመሰግናለን በማለት ተናግረዋል።

አበረታች ቅመም ጉዳይ የስፖርቱ በሽታ እየሆነው መጥቷል ስፖርቱ እስከ አሁን እንደ ሀገር የምንታወቀው ተወዳድረን በማሸነፍ ውጤት በማምጣት ባንድራችንን ከፍ አድርገን በማብሎብለብ ነው የምንታወቀው አሁን ሁሉም ስፖርቶች ከኛ እየሸሹ መጥቷል ይህንን ችግር መከላከልና መቆጣጠር ካልቻልን አትሌትቲክሱንም በአጭር ጊዜ ከእጃችን እናጠዋልን እንደ ሌሎች ስፖርት ገና ዳዴ ብለን መጀመር ወደ ምንችልበት ደረጃ መውረዳችን የማይቀር ነው የሚሆነው ስለዚህ ሁላችንም ተባብረን ዶፒንግን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አይናችንን ሳንከድን ከስፖርት ልማቱ እኩል ማከናወን እንደሚገባ ክቡር ዳይሬክተሩ አሳስቧል ፡፡

አክሎም የአበረታች ቅመሞች ጉዳይ ችላ የምንለው አይደለም ሌላ የስፖርት ልማት ካከናወን ቡኋላ በሁለተኛ ደረጃ ይደርሳል ብለን የምናስበው አይደለም
በየቀኑ ስፖርተኛን እየበላ ነው የሚሄደው በየቁኑ ስፖርቱን እያጠፋ ነው የሚሄደው እንዲሁም የስፖርቱን ተአማኒነት እየቀነሰ ነው የሚሄደው ህዝብ የማይደግፈውና የማይከተለው ስፖርት ደግሞ ስፖርት አይደለም ስለዚህ ስፖርቱ ተአማኒነቱ እንዲያስቀጥል ማድረግ መቻል ይኖርብናል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ዶፒንግን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ማድረግ መቻል አለባችሁ ክልሎችም የሚያስፈልገው ስልጠና እና የመከላከል ሥራ መስራት ይጠበቅባችኋል እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላትም የበኩላቸውን ሚና መወጣት አለባችሁ የአበረታች ቅመሞች ጉዳይ የአንድ ተቋም ሥራ አለመሆኑ በመገንዘብ ሁላችንም ርብርብ ሊናደርግ ይገባል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፏል፡፡

በመቀጠልም የፀረ- የአበረታች ቅመሞችን የመከላከል እና መቆጣጠር እንቅስቃሴ፣ የሚያስከትሉ ጉዳቶች እና በህግ ማዕቀፍ በአቶ ፈለቀ ዋለልኝ እና በአቶ ንጋቱ መኮንን ለተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ገለጻ አድርጓል ።
በቀረበው  ገለጻ ከተሳታፊዎች ጥያቄ ና አስተያየት ቀርቦ በአመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።

By Ermias