የኢትዮጵያ የፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት የስፖርት ትምህርት ስልጠና ዘርፍ አመራሮች ጋር በዛሬው ዕለት የጋራ ውይይት አድርጓል።
ግንቦት 30/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ የፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የበላይ አመራሮች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄዷል።
የውይይቱ ዓላማ በፀረ አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴ ዙሪያ የሚያጠነጥን ሲሆን በቀጣይ በተቀናጀ መልኩ እንዴት በጋራ መስራት እንደሚገባ የሚያመላክት ነው ።
ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል በውይይቱ መድረኩ ያነሱ ሃሳብ በአበረታች ቅመሞች በአሁን ጊዜ በአስከፊ ሁኔታ ላይ በመሆኑና መከላከሉ ላይ ያለው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ክልሎችና ከተማ መስተዳድርች የራሳቸውን ድርሻ ወስደው መንቀሳቀስ እንደሚገባ ገልፀዋል።
አክለውም የፀረ አበረታች ቅመም እያደረሰው ያለው ተፅዕኖ የመከላከልና የመቆጣጠር እንቅስቃሴ በተወሰነ አካል ብቻ የተገደበ በመሆኑ በዚህ መጠን ውጤት ሊመጣ እንደማይቻል በመገንዘብ እንደ ሀገር በየደረጃው ሀላፊነት መወጣት ግዴታ እንደሚሆን ገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልዩ የሚያደርገው ካለበት ነባራዊ ሀኔታዎች አብዛነኛውን የህግ ጥሰቶች የሚፈፀምበት በመሆኑ ልዩ ትኩረት በመስጠት የመከላከል እና የመቆጣጠር የሁላችንም ግዴታ በመሆኑ
በተቀናጅ መልኩ መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡
አክሎውም በፀረ-አበረታች ቅመሞች የመከላከል እንቅስቃሴዎች እንዳሉ ሆነ በቂ አለመሆናቸውና የሰው ሀይል ያለው መዋቅሩ እና ባለድርሻ አካላትን አቀናጅቶ መምራት እንደ ከተማ አስተዳደር መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በቢሮ ሀላፊ ደረጃ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ሀላፊ ኮሚሽነር ተስፋዩ ኦሜጋ እንዳሉት ባለስልጣን ጋር በተቀናጀ ሁኔታ የፀረ- አበረታች ቅመሞች ለመከላከል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት መስራት እንደሚያስፈልግ እና በከተማ መስተዳድር መስተካከል ያለባቸው ጉዳዩች እያስተካከልን በባለቤትነት እንሰራለን ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በቀጣይ በቅንጅት መስራት ይኖርብናል በማለት ውይይቱ አጠናቋል ።

By Ermias