ለመቻል ስፖርት ክለብ አትሌቶች እና ለአትሌት ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
ህዳር 3/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ችግር በዘላቂነት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሰፊ ትኩረት ሰጥቶት በየጊዜው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ለመቻል ስፖርት ክለብ አትሌቶች ፣ አሰልጣኞች እና ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰቷል።
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ በስልጠና መድረክ ላይ ካስተላለፉት መልዕክት:- ዶፒንግ በአሁኑ ሰዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲሁም በሀገራችን ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ጠቁመዋል።
በመጀመሪያ ደረጃ ስፖርተኛ መሆን ስትወስኑ ማወቅ ያለባችሁ ስለ አበረታች ቅመሞች በቂ ግንዛቤ ሊኖራችሁ ይገባል ካለበለዚያ ልፋታችሁ፣ ጥረታችሁን በዜሮ የሚያባዛ ነው ብለዋል ።
ክብርት ዳይሬክተሯ አያይዞም በየትኛውም ስፖርት መድረክ ለመወዳደር ስፖርቱ የሚያስፈልገው ፎርማሊቲ ብታሟሉም ከዶፒንግ ነፃ እስካልሆናችሁ ድረስ ትርጉም አልባ መሆኑን ጠቁመዋል ።
በመጨረሻም ክብርት ዳይሬክተሯ ካስተላለፉት መልዕክት በዋናነት ስለ አበረታች ቅመሞች በቂ እውቀት ሊኖራቸው እንደሚገባ በመግለፅ
እራሳቸውን ከአበረታች ቅመሞች መጠበቅ እንደሚገባቸው ገልፀው ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉ በማሳሰብ ስልጠናው አስጀምረዋል።
ስልጠናው በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦች ፣ የተከለከሉ ንጥረ ነገሮች እና ዜዴዎች ፣ የሚያስከትለውን ጉዳት እና የህግ ማዕቀፎችና የአሰራር ስርዓቶች እንዲሁም በምርምር እና ቁጥጥር ሂደት ያተኮረ ነበር።

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *