ለስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር ባለሞያዎች (Sample Collection Personnel’s) የአቅም ግንባታ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል ።
ሚያዝያ 22/2017 ዓ/ም
አዳማ
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ለስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር ባለሙያዎች በዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር እና አጠቃላይ እንቅስቃሴ ዙሪያ በአዳማ ከተማ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል ፡፡
ስልጠናው ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በDCO Central ፣ Testing procedure፣ Urine and blood sample collection in competition out of competition፣ notification of athlete testing and legal procedure፣ Roll of DCO ,BCO on intelligence እና Irregularity about testing ዙሪያ ያተኮረ ሙያዊ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል በመድረኩ እንደተናገሩ የዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር ባለሙያዎች በበጎ ፈቃደኝነት ለሀገራችሁ እና ለህዝባችሁ የዜግነት ሃላፊነትን በአግባቡ አስተዋፅኦ ማበርከት በመቻላችሁ ምስጋና ይገባችዋል ብለዋል፡፡
አያይዘውም የዚህ የስልጠና ዋነኛ ዓላማ የምርመራ ሥራዎችን ጥራት ያለው ሥራ መስራት እንደሚያስፈልግ እና የአለም አቀፍ የአሰራር ስርዓቶችን እና ህጉችን ሙሉ በሙሉ በሚገናኙበት መልኩ የምርመራ ሥራዎች ጥራቱን ያደገና ሙያዊ የሆነ ሥራ እየተሰራን መሄድ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው ሙያተኞች የእውቀት ደረጃቸውን እያደገ መሆድ ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል።
አክለውም የኢትዮጵያ ሻምፒዮና በዚህ ዓመት በልዩ ሁኔታ እየተሰራ መሆኑና ከአለም አትሌቲክስ ጋር በቅንጅት በጋራ በማቀድ ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልፀው ሙያተኞች ለሚሰሩት ሥራ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የምርመራ ሥራዎች የአለም አቀፉን የአሰራር ስርዓት በመከተል ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ አሳስቧል።
በመጨረሻም በቀጣይ የቶኪዮ ዓለም ሻምፒዮና ሥራ ቁርጠኝነት የሚፈልግ ሥራ ስለሆነ ሙያተኞች ራሳቸውን ከወዲሁ እንዲያዘጋጁ ክቡር ዳይሬክተሩ መልዕክት አስተላልፏል።