ስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላት እንደ ባለቤት የአበረታች ቅመሞች የመከላከያና የመቆጣጠር ስራ ቀዳሚ አጀንዳ አድርጎ መውሰድ እንደሚገባ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መኮንን ይደርሳል ተናግረዋል።

መስከረም   14/2018 ዓ.ም
አዳማ
የኢትዮጵያ ፀረ- አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላት  ለተውጣጡ  አመራሮችና ባለሙያዎች የፀረ-አበረታች ቅመሞች የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የልምድ ልውውጥ እያተካሄደ ነዉ ።
የኢትዮጰያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል  በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት  አበረታች ቅመሞች ጉዳይ በአለም አቀፍ ደረጃ የስፖርት ችግር እየሆነ መምጣቱና ስፖርቱን በከፍተኛ ፍጥነት ስጋት ላይ እየጣለ ያለ ጉዳይ ነዉ ብለዋል ።
በአለም አቀፍ ተቋማት ፣አለም አቀፍ የስፖርት ማህበራት እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የመጀመሪያ ተግዳሮት ና አንገብጋቢ ጉዳይ በመሆኑ በአለም አቀፍ ደረጃ በቂ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን አቶ መኮንን ጠቁመዋል።
አበረታች ቅመም ስፖርተኛች ሲጠቀሙ የዜጎች የጤና ችግር አልፎ በማህበረሰቡ ጫናና እንደ ሀገር የሚመጣ ጫና ከፍተኛ እየሆነ በመምጣቱ በቂ የሆነ ግንዛቤ በመስጠት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል ።
ክቡር ዳይሬክተሩ አክለውም አበረታች ቅመም እንደ ሀገር ኢትዮጵያ ገፅታ የሚያጠለሹ መሆኑን ስለታመነበት ችግሩን ከጅምሩ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሰፊ ርብርብ ሲደረግ መቆየቱ አሳውቋል።
ስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላት እንደ ባለቤት የአበረታች ቅመሞች የመከላከያና የመቆጣጠር ስራ ቀዳሚ አጀንዳ አድርጎ መውሰድ እንደሚገባ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
የአበረታች ቅመም ህግ ጥሰት የሚፈፀም አካል በስፖርቱ ብቻ ሳይሆን ሀገርንም ስለሚጎዳ የዜጎችን ጤና አደጋ ላይ የሚጥል ስለሆነ በወንጀል ጭምር ተጠያቂ እንደሚሆን ተገለፀ ።
የስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላት ዶፒንግ ጉዳይ ከስፖርት ስልጠና እኩል ትኩረት በመስጠት በስልጠና ማንዋሎች ውስጥ ተካቶ መስራት እንደሚገባ አቶ መኮንን አሳስበዋል ።
በመድረኩ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽንሰ ሃሳብ ፣ የአበረታች ቅመሞች ምርመራ ሂደቶች እና አሰራር ስርአት ላይ ጥልቅ ግንዛቤ እንዲጨቡጡ ሰነዶች እንዲሁም ጥሩ የሆነ ልምድ ያላቸው አራት ማዕከላት ተሞክሯቸው በማቅረብ የጋራ ውውይት ተደርጎበታል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *