በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ክለብ ስር ታቅፈው የሚገኙ አትሌቶች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ  ።

ታህሳስ 8/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ክለብ ጋር በመተባበር  በስሩ ታቅፈው የሚገኙ  አትሌቶች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

የባለስጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ በስልጠና መድረክ ላይ ካስተላለፉት መልዕክት፦
መንግሥት ልዩ ትኩረት ሰጥቶት  በመደበኛ ትምህርት ካሪኩለም   በስምንት /8 / ትምህርት ዘርፎች የአበረታች ቅመሞች ምንነትና የሚያስከትለው ጉዳት የሚለውን ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት መማሪያ መፅሐፍት ውስጥ እንዲካተት  አድርጎ እየተሰጠ መሆኑን ገልፀው በኮሌጆችና በከፍተኛ ትምህርት ደረጃም ተካቶ እንዲሰጥ ቅድመ ዝግጅት ስራ እየተሰራ መሆን አሳውቀዋል።

አክለውም ፌዴሬሽኖች የስፖርት ክለባት የዶፒንግን ጉዳይ በማሰልጠኛ ማኑዋላቸው በማካተት በቴክኒክ ስልጠና ጎን ለጎን በየጊዜው ለስፖርተኞች ግንዛቤ መስጠት  እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

አትሌቶች በፀረ-አበረታች ቅመሞች ዙሪያ ሁሌም ተገቢውን ዕውቀት ኖሯችሁ ከሚደርስባችሁ ዘርፈ ብዙ ጉዳቶች እራሳቸው መጠበቅ  እንደሚገባ ክብርት ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡

በዋናነት ስልጠናው በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦች ፣ የተከለከሉ ንጥረ ነገሮች እና ዜዴዎች ፣ የሚያስከትለውን ጉዳት እና የአሠራር ስርዓቶች እንዲሁም በምርመራና ቁጥጥር ሂደት ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን ገለጻውንም ያደረጉት በአቶ መንግስቱ የምሩ እና በወ/ሮ ወይንሸት ሙሉጌታ ናቸው።

በመጨረሻም በቀረበው ገለጻ  ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው የተቋሙ  ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት  ወ/ሮ  ፋንታዬ ገዛኸኝ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *