በኦሮሚያ ክልል ለሚገኙ ስፖርት ፌዴሬሽን አመራሮች እና ባለሙያዎች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ እንዲፈጠር ተደርጓል።
ህዳር 28/2017 ዓ.ም
ሱሉልታ
የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በሱልልታ ከተማ የኦሮሚያ ስፖርት ፌዴሬሽኖች ጠቅላላ ጉባኤ መድረክ በመገኘት ለስፖርት ፌዴሬሽን አመራሮች እና ባለሙያዎች በዶፒንግ ዙርያ ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል።
ስልጠናውን የአበረታች ቅመሞች መከላከል ግንዛቤ እና ህዝብ ንቅናቄ ሥራ አስፈፃሚ ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሮ ወይንሸት ሙሉጌታ የዶፒንግን መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦች ፣ የተከለከሉ ንጥረ ነገሮች እና ዜዴዎች ፣ በአሰራር ስርአቶች ዙሪያ ገለጻ ተደርጓል።




