በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ ላይ የተዘጋጀው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታ ውድድር ላይ ሰፊ የፀረ አበረታች ቅመሞች የግንዛቤ ማስጨበጫና የህዝብ ንቅናቄ ኘሮግራም ተካሄደ።
ሰኔ 16/2017 ዓ.ም
ጅማ
የኢትዮጵያ ፀረ -አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከሰኔ 10 – 19 /2017 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እየተካሄደ በሚገኛው 6ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታ ውድድር ተሳታፊ አትሌቶች፣ አሰልጣኞች፣ የስፖርቱን ማህበረሰብ በማሳተፍ በፀረ-አበረታች ቅመሞች/ ዶፒንግ ዙሪያ ሰፊ ግንዛቤ በማሳደግ እና ንቅናቄ በመፍጠር Outreaching ፕሮግራም በስፋት ተካሄዷል።
ፕሮግራሙ አዝናኝ በሆነ መልኩ በስፖርት አበረታች ቅመሞች መሰረታዊ ሃሳብና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ግንዛቤ እንዲጨብጡ የሚያስችሉ ጥያቄና መልስ ውድድርና አዝናኝ በሆኑ ጨዋታዎችና የተለያዩ የህትመት ውጤቶች ለታዳሚዎች የተሰራጨ ሲሆን እንዲሁም አስተማሪ መልዕክት የያዙ የፀረ-ዶፒንግ መልዕክቶች በውድድር ስፍራ በማይክ እንዲተላለፍ በማድረግ ሰፊ ስራዎችን መስራት የተቻለ ሲሆን በዚህም የስፖርቱ ማህበረሰብ እራሳቸውን ከስፖርት አበረታች ቅመሞች መጠበቅ የሚችሉበትን ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል፡፡

