በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስፖርት አበረታች ቅመሞች ዙሪያ የግንዛቤና ንቅናቄ መርሃ ግብር ተጀምሯል ።
ህዳር 11/2017 ዓ.ም
ጂንካ
የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ችግር በዘላቂነት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሰፊ ትኩረት ሰጥቶት በየጊዜው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት ላይ የሚገኝ ተቋም ነው።
በዚሁም መሠረት በዛሬው ዕለት ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጋር በመተባበር የኣሪ ዞን በጂንካ ከተማ ለሚገኙ የስፖርት ዘርፍ አመራሮች፣ ታዳጊ ኘሮጀክት አትሌቶች እና ድጋፍ ሰጪ አካላት እንዲሁም የወርልድ ቴኳንዶ፣ ማርሻል አርት ስፖርተኞች ፣ አሰልጣኞችና ድጋፍ ሰጪ አካላት በጂንካ አትሌቲክስ ማዕከል በተለያየ ሰዓት በስፖርት አበረታች ቅመሞች ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
የባለስጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ በስልጠና መድረክ ላይ ካስተላለፉት መልዕክት ተቋማችን የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ችግር በዘላቂነት ለመከላከልና ለመቆጣጠር በየጊዜው ስልጠና በመስጠት ላይ እንደሆነ ገልፀው ክልሎችም የዜጎችን ጤንነት የመጠበቅ ከፍተኛ ሐላፊነት እንዳለባቸው ገልፀው ስፖርተኞችም ስለ አበረታች ቅመሞች በቂ እውቀት ሊኖራቸው እንደሚገባ እና እራሳቸውን ከአበረታች ቅመሞት መጠበቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
አክለውም በስልጠና ማእከሉ በስልጠና ማልዋል
በመጨረሻም ክብርት ዳይሬክተሯ ካስተላለፉት መልዕክት በስልጠና ማዕከላት በስልጠና ማንዋላቸው ውስጥ አበረታች ቅመሞች አካተው በመደበኛነት እንዲያስተምሩ ገልፀው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ተናግሯል።
ስልጠናው በዋናነት ስልጠናው በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦች ፣ የተከለከሉ ንጥረ ነገሮች እና ዜዴዎች ፣ የሚያስከትለውን ጉዳት እና የህግ ማዕቀፎችና የአሰራር ስርዓቶች እንዲሁም በምርምር እና ቁጥጥር ሂደት ዙሪያ ለሰልጣኞቹ ሰፋ ያለ ገለጻ ተደርጓል።







