በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እየተካሄደ ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር እንደቀጠለ ነው፡፡
ህዳር 13/2017 ዓ.ም
ኮንሶ
በስፖርት አበረታች ቅመሞች ዙሪያ የግንዛቤና ንቅናቄ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጋር በመተባበር ኮንሶ ዞን በካራት ከተማ ለሚገኙ ለስፖርት ዘርፍ አመራሮች ፣ የወርልድ ቴኳንዶ ሰልጣኞች እና አሰልጣኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ በስልጠና መድረክ ላይ ካስተላለፉት መልዕክት ተቋማችን አበረታች ቅመሞች ለመከላከል ሰፊ ትኩረት በመስጠት መድረኮችን በመፍጠር የስፖርቱን ማህበረሰብና የሚመለከተው የህብረተሰብ ክፍል በተለይም ስፖርተኞች እና ስፖርቱን የሚመሩ አካላት ግንዛቤ እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል።
አሰልጣኞች በየስልጠና ማንዋላቸው ውስጥ አበረታች ቅመሞች አካተው በመደበኛነት ለስፖርተኞች ግንዛቤ እንዲያገኙ ማድረግ እንዳለባቸው ጠቁመው ስፖርተኞችም እራሳቸውን ከአበረታች ቅመሞች መጠበቅ እንደሚገባቸው ገልፀው ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉ በማሳሰብ መርሃ ግብሩን አስጀምረዋል።
ስልጠናው በዋናነት በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦች ፣ የተከለከሉ ንጥረ ነገሮች እና ዜዴዎች ፣ በአሰራር ስርአቶች፣ የሚያስከትለውን ጉዳት እና ባሉት ሕግና ደንቦች እንዲሁም በምርምር እና ቁጥጥር ሂደት ዙሪያ ለሰልጣኞች ገለጻ እና ማብራሪያ ተደርጓል።

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *