በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ዩኒቨርስቲ የሚገኙ የስፖርት ሳይንስ ተማሪዎች እና መምህራኖች እንዲሁም የጤና እግር ኳስ ቡድን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
ህዳር 12/2017 ዓ.ም
ጂንካ
የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጂንካ ዩኒቨርስቲ የሚገኙ የስፖርት ሳይንስ ተማሪዎች እና መምህራኖች እንዲሁም የጤና እግር ኳስ ቡድን በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ግንዛቤ እንዲፈጠር ተደርጓል።
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ ካስተላለፉት መልዕክት ተቋማችን አላማ አድርጎ የሚሰራቸው ሥራዎች አበረታች ቅመሞችን መከላከልና መቆጣጠር ሲሆን በተለያዩ መድረኮች ግንዛቤ በመፍጠር ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑና አስፈላጊውን ምርመራ እና ቁጥጥር እያካሄደ በመሆኑ እንዲሁም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በተዋቀረ ቡድን ክትትል እና ቁጥጥር ሥራ እያከናወነ እንደሆነ በንግግራቸው ገልፀዋል።
ክብርት ዳይሬክተሯ አክለውም አበረታች ቅመሞች በተመለከተ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፣በ2ተኛ ደረጃ ት/ት ቤት እንዲሁም በስፖርት ማዕከላት ውስጥ ትኩረት እየተሰጠው እንዳልሆነና ዶፒንግ ግን እንደ ሀገር የሚያስከትለው ጉዳቶች ከፍተኛ በመሆኑ አትሌቶች እንዲሁም በስፖርቱ ዙሪያ የሚገኙ ሞያተኞች ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባ ገልጿል ።
በመጨረሻም የስፖርት ሳይንስ መምህራኖች ስፖርቱን ስለ አበረታች ቅመሞች በደንብ አድርጋችሁ እንዲያውቁ የማድረግ ከፍተኛ ኃላፊነት በእናንተ እንጠብቃለን እንዲሁም ስፖርት ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ እውቀቱን ይዛችሁ በምትሰማሩበት የስፖርት መስክ ሁሉ አበረታች ቅመሞች ምን ያህል ጎጂ እንደሆነና የሀገርን ገፅታ እንደሚያጠፋ እና ትውልድን እንደሚጎዳ ማሳወቅ እንደሚገባ ምክትል ዳይሬክተሯ ጠቁመዋል ።
ስልጠናውን ከኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የአበረታች ቅመሞች መከላከል ግንዛቤ እና ህዝብ ንቅናቄ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፈለቀ ዋለልኝ በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦች ፣ የተከለከሉ ንጥረ ነገሮች እና ዜዴዎች ፣ በአሰራር ስርአቶች፣ የሚያስከትለውን ጉዳት እና ባሉት ሕግና ደንቦች እንዲሁም በምርምር እና ቁጥጥር ሂደት ዙሪያ ገለጻ እና ማብራሪያ አድርገዋል ።





