ተቋሙ የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ ።
ጥር 4/2017 ዓ.ም
አዳማ
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ፣ የስድስት ወራት የክትትል እና ድጋፍ ግብረ መልስ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር እቅድ ላይ የተቋሙ አመራሮች እና አጠቃላይ ሰራተኞች በተገኙበት በአዳማ ከተማ የጋራ ውይይት አካሄዷል ፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል በመድረኩ ካስተላለፉት መልዕክት በውይይታችን ወቅት በደንብ አጠንክረን መወያየት እና ሀሳብ መለዋወጥ ያለብን እንደ ተቋም የምንሰራቸው ሥራዎች ባለፉት 6 ወራት እያከናወን ያሉ ግቦች እና እየፈፀምናቸው ያሉ ተግባራት ወደ ዋና ራዕይያች የሚወስዱ መሆናቸው በደንብ በጥልቀት መወያየት ያስፈልጋል ብለዋል።
በተቁሙ የሚሰሩ ስራዎችን ሁሌም በአለም አቀፍ ህጎችና የአሰራር ስርዓቶች መሰረት ባደረጉ መልኩ መከናወን ይኖርባቸውል በማለት አቶ መኮንን ገልፀዋል ።
አክለውም ተቋማችን የራሱ ልዩ ባህል ሊኖረው ይገባል መገለጫ ሊሆን የምንፈልገውን ዲሞክራሲያዊ የሆነ ተቋም እንዲኖር እና በወንድማማችነት እና እህትማማችን እርስ በርስ በመተሳሰር የሚደጋገፉ እና አንዱ የአንዱን ጉድለት የሚሞላ መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል።
በመጨረሻም ዳይሬክተሩ እንደተናገሩት የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችን በአገልግሎት አሰጣጣችንም እንዲሁም በምንሰራቸው ሥራዎች ውጤታችን እየጨመርንና እያሳደግን መሄድ ያስፈልጋል በማለት ተናግሯል።
በመድረኩም በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ሪፖርት የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ በወ/ሮ ስርጉት በየነ፣ የስድስት ወራት የክትትል እና ድጋፍ ግብረ መልስ በአቶ አዛናው መኳንንት እንዲሁም የመልካም አስተዳደር እቅድ በአቶ መስፍን ኩራባቸው አማካኝነት ቀርበው የጋራ ውይይት ተደርጎባችዋል፡፡
በመጨረሻም ክቡር ዳይሬክተሩ እንደ ተቋም የታዩ መልካም አፈጻጸሞችን በተገቢው ሁኔታ በማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀው በቀጣይ ትኩረት ተስጥቶባቸው ሊሰሩ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል ።

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *