አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የሚገኙ 2ተኛ ዓመት የስፖርት ሳይንስ ተማሪዎች እና መምህራኖች እንዲሁም የቨሊቮል ቡድን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
ህዳር 14/2017 ዓ.ም
አርባ ምንጭ
የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የሚገኙ የስፖርት ሳይንስ ተማሪዎች እና መምህራኖች እንዲሁም የቨሊቮል ቡድን በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ እንደተናገሩት በዘላቂነት አበረታች ቅመሞች ለመከላከል ይረዳል ተብሎ በተቋማችን እምነት የተጣለበት በትምህርት ሚኒስቴር ጋር መሆን በመደበኛ ትምህርት ከ5-12 በ8 ዓይነት ውስጥ ተካቶ አበረታች ቅመሞች በመደበኛነት ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልፀው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ጉዳዩ ለሚመለከተው የትምህርት አይነት ውስጥ እየተካተተ እንዲሰጥ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም ኤጄንሲ ጋር በመነጋገር ጥረቶች እንደተጀመረ ጠቁመዋል።
የዩኒቨርስቲ ተቋማት ስልጠና መስጠት ያስፈለገበት ምክንያት መምህራኖች የስፖርት ባለሙያዎችን የምታፈሩ በመሆናችሁ ለዶፒንግ ትኩረት ሰጥታችሁ በምታስተምሩት ጊዜ ግንዛቤ ማስያዝ ይኖርባችኋል በማለት ተማሪዎቹ ደግሞ አበረታች ቅመሞች ጎጂነት አውቃችሁ ነገ ወደምትሰማሩበት ህብረተሰብ ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት ቀላል የሚባል ባለመሆኑ ትልቅ ሀላፊነት ያለባችሁ በመሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፍንጭ ከሰጠናቹሁ አንብባችሁ ችግሩን የራሳችሁ አድርጋቹሁ ትከላከላላችሁ የሚል እምነት አለን በማለት ክብርት ዳይሬክተሯ መልዕክት አስተላልፏል።
ስልጠናው በዋናነት በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦች ፣ የተከለከሉ ንጥረ ነገሮች እና ዜዴዎች ፣ በአሰራር ስርአቶች፣ የሚያስከትለውን ጉዳት እና ባሉት ሕግና ደንቦች እንዲሁም በምርምር እና ቁጥጥር ሂደት ዙሪያ ያተኮረ ነበር ።

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *