Read Time:23 Second
(ግንቦት 12 /2013 ዓ.ም) በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ በሲዳማ ብሄራዊ ክልል በሐዋሳ ከተማ ለሚገኙት በቤትኪንግ ኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ ላይ እየተሳተፉ ላሉት የእግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች እና የህክምና ባለሞያዎች የሚሰጠው ስልጠና እና የንቅናቄ መድረክ መካሄዱን ዛሬም ቀጥሏል፡፡
በከሰአቱ የስልጠና መርሃ -ግብር ላይ ለአዳማ ከተማ የእግር ኳስ ቡድን ተጫዋቾች እና የህክምና ባለሙያዎች ስልጠናው ተሰጥቷል ፡፡
የክለቡ ተጫዋቾች እና የስፖርቱ ባለሞያዎችም ችግሩን በመከላከልና ከአበረታች ቅመሞች እራሳቸውን በመቆጠብ ዶፒንግን በመዋጋት ረገድ የበኩላቸውን ገንቢ ሚና መጫወት እንደሚጠበቅባቸው ተጠቁሟል።