ወላይታ ሶዶ ላይ በተዘጋጀው የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር ላይ ሰፊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች የግንዛቤ ማስጨበጫና የህዝብ ንቅናቄ ፕሮግራሞች ተካሂደዋል።

Williams Brown

Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipisicing elit. Dolor, alias aspernatur quam voluptates sint, dolore doloribus voluptas labore temporibus earum eveniet, reiciendis.

Tags


ወላይታ ሶዶ ላይ በተዘጋጀው የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር ላይ ሰፊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች የግንዛቤ ማስጨበጫና የህዝብ ንቅናቄ ፕሮግራሞች ተካሂደዋል።
ተተኪ ስፖርተኞች ወደ ኢሊት ደረጃ ለመሸጋገር በስፖርቱ ከሚኖራቸው ክህሎት ባለፈ በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ በቂ የሆነ እውቀት እንዲኖራቸው ማድረግና ስነ-ምግባራቸውን ማነፅ ያስፈልጋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከውድድሩ ጎን ለጎን ሊከናወኑ የሚችሉ የተለያዩ ፕሮግራሞችን በመቅረፅ ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን በዋናነት ለስፖርተኞች፣ ለባለሞያዎች እና ለአመራሮች የገፅ ለገፅ ስልጠናዎች፣ የOutreaching እና የSocial Campaign ፕሮግራሞችም በስፋት ተካሂደዋል።
እነዚህ ፕሮግራሞች የተደራሽ አካላትን (Target Groups) ባህሪ መሰረት ባደረገ መልኩ የተቀረፁና አዝናኝ በሆነ መልኩ የተካሄዱ በመሆናቸው ስፖርተኞችን ጨምሮ የስፖርቱን ማህበረሰብ በስፋት ማሳተፍ እንዲሁም ከፍተኛ ግንዛቤና ሰፊ ንቅናቄ መፍጠር ተችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *