የሴቶች ሚና ተቋም ውስጥ አስፈላጊነቱ የማይተካ መሆኑ ተጠቆመ ።
ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም
አዳማ
በአዳማ ከተማ ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው ዕለትም የቤተሰብ ሕግ ዙሪያ በአበረታች ቅመሞች ውጤት አስተዳደር ሕግ ትግበራና አፈፃፀም መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ መኮንን ለሴት ሰራተኞች ሰፋ ያለ ገለጻ እና ውይይት በማድረግ ስልጠናው ተጠናቋል።
ባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል በመዝጊያ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን የሴቶች ሚና ተቋም ውስጥ በጣም አስፈላጊና የማይተካ ነው ይሄን ለማለት ብቻ ሳይሆን በተግባር ያየንበት ስለሆነ በሴቶች የሚመሯቸው የስራ ክፍሎች ውጤት ሲያመጡ በተግባር አይተናል ስለዚህ ሴቶች ወደ ኋላፊነት ሲመጡ ስራቸውን በታማኝነት መስራት ስለሚችሉና ቁርጠኝነቱ ስላላቸው በብቃት መፈፀም ይችላሉ ስለዚህ ሴቶችን እያበቁ መሄድ ቅድሚያ እየሰጠን መሄድ ለተቋሙ ጠቃሚ መሆኑ ገልጿል ።
አክለውም የሴቶች ፎረሙ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንደ ተቋም አስፈላጊውን እገዛና ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀው የፎረሙ አመራሮች ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
ለስልጠና የተመረጡት ርዕሶች ጥሩ በመሆናቸው እና ለቀጣይ እንደዚህ አይነት ርዕሶች በመምረጥ ሞያተኞችን በመጋበዝ ስልጠናዎችን እንድታገኙ ጥረት እናደርጋለን በማለት ዳይሬክተሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡