የስፖርት ሳይንስ ተማሪዎች ፣ መምህራኖችና የስፖርት ዘርፍ አመራሮች በፀረ አበረታች ቅመሞች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
ህዳር 16/2017 ዓ.ም
ወላይታ ሶዶ
ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጋር በመተባበር
የግንዛቤና ንቅናቄ መርሃ ግብር የቀጠለ ሲሆን በዛሬው ዕለት ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የሚገኙ የስፖርት ሳይንስ ተማሪዎች እና መምህራኖች እንዲሁም የስፖርት ዘርፍ አመራሮች በፀረ- አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ እንደተናገሩት
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ለሀገራችን ስጋት ሆኖ እየተሸጋገረ ያለውን አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሰፊ ትኩረት ሰጥቶት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል ።
አክለውም አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ስፖርቱን ሊጎዳና የሚያጠፋ መርዝ በመሆኑ በቅድሚያ እውቀቱ ሊኖራችሁ ግድ ነው ምክኒያቱም እናንተ የስፖርቱ ማህበረሰብ በመሆናችሁ መርዙን ማስወገድ እና በስፖርቱ ላይ መከላከል የዘርፉ ባለቤትነትን የወሰዱ አካላት ግዴታ ነው ብለዋል ።
በአጠቃላይ አበረታች ቅመሞች ማለት ጥረታችንን ልፋታችንን በዜሮ የሚያባዛ በመሆኑ ስለ አበረታች ቅመሞች እውቀቱ ኖራችሁ ወደ ምትሰማሩበት ሥራ መስክ በመከላከል የዜግነት ሀላፊነት አለባችሁ በማለት ክብርት ዳይሬክተሯ መልዕክታቸውን አስተላልፏል።
ስልጠናው በዋናነት በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦች ፣ የተከለከሉ ንጥረ ነገሮች እና ዜዴዎች ፣ በአሰራር ስርአቶች፣ የሚያስከትለውን ጉዳት እና ባሉት ሕግና ደንቦች እንዲሁም በምርምር እና ቁጥጥር ሂደት ዙሪያ
ሲሆን ገለጻውንም ያደረጉት ከኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የአበረታች ቅመሞች መከላከል ግንዛቤ እና ህዝብ ንቅናቄ መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፈለቀ ዋለልኝና ለሰልጣኞች ሰፋ ያለ ገለጻ አድርጓል ።

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *