የኢትዮጵያ ሱፐር ሊግ እግር ኳስ ክለቦች እና ለጦና ቦክስ ቡድን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል ፡፡
ህዳር 17/2017 ዓ.ም
ወላይታ ሶዶ
የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት እያካሄደ ያለው የግንዛቤና ንቅናቄ መርሃ ግብር በዛሬው እለትም ለአትሌቶች እና ለአሰልጣኞች ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል ፡፡
የኢትዮጵያ ሱፐር ሊግ እግር ኳስ ክለብ ውድድር ለመሳተፍ ወላይታ ሶዶ ለተገኙ የጂንካ እግር ኳስ ቡድን፣ የቤኒሻንጉል እግር ኳስ ቡድን እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ /አ.አ/ እግር ኳስ ቡድን እንዲሁም ጦና ቦክስ ቡድን በፀረ አበረታች ቅመሞች /ዶፒንግ/ ግንዛቤ መፍጠሪያ ስልጠና መስጠት ተችሏል፡፡
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ በስልጠና መድረክ ላይ ካስተላለፉት መልዕክት:- አበረታች ቅመሞች ትውልድን የሚጎዳና ለስፖርቱ የሚያጠፋ መርዝ መሆኑን አውቃችሁ ካልተከላከላችሁ በስተቀር ስፖርቱ ትርጉም እንደሌለውና ውጤታማ መሆን እንደማይቻል ገልፀዋል ።
አክለውም አትሌቶች ከስፖርት አበረታች ቅመሞች እራሳቸውን መጠበቅና ተፈጥሯዊ የሆኑ ምግቦች በመመገብ እንደሚገባቸውና ሊደርስባቸው ከሚችሉ የጤናና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ከወዲሁ መጠንቀቅ እንደሚገባቸው አሳስበዋል ።
የስፖርት ማዕከላት በማሰልጠኛ ማንዋል ውስጥ ስለአበረታች ቅመሞች አካተው አትሌቶች ግንዛቤ እንዲያገኙ ማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው ክብርት ዳሬክተሯ ተናግረዋል።
በዋናነት ስልጠናው በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦች ፣ የተከለከሉ ንጥረ ነገሮች እና ዜዴዎች ፣ የሚያስትሉትን ጉዳቶች ፣ በሕግና ደንቦች እንዲሁም በምርምር እና ቁጥጥር ሂደት ዙሪያ ገለጻ ተደርጓል።

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *