የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የ2017 ዓ.ም 1ኛ ሩብ አመት የሥራ አፈጻጸም እና የሀገሪቱን የመቶ ቀን የለውጥና ኢኮኖሚ ሪፎርም አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሄደ፡፡
ጥቅምት 18/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የ2017 ዓ.ም 1ኛ ሩብ አመት የሥራ አፈጻጸም እና የሀገሪቱን የመቶ ቀን የለውጥና ኢኮኖሚ ሪፎርም አፈፃፀም ላይ የባለስልጣኑ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት በተቋሙ አዳራሽ ውይይትና ግምገማ አካሂዷል ፡፡
የተቋሙ የ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ አመት የሥራ አፈጻጻም ሪፖርት በስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ባለሙያ አቶ አዘናው መኳንንት እንዲሁም የ2017 የመጀመሪያ የሀገሪቱን የመቶ ቀን የለውጥና ኢኮኖሚ ሪፎርም አፈፃፀም የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል አማካኝነት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል ፡፡
በቀረቡት ሪፖርቶች ዙሪያ ከሰራተኛው ጥያቄ ና አስተያየት ቀርቦ በበላይ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰቶበታል
በቀጣይ ትኩረት ተስጥቶባቸው ሊሰሩ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

By Ermias