የኢትዮጵያ የፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ከወጣቶች ስፖርት ቢሮ አመራሮች ጋር የጋራ ውይይት አድርጓል።
ህዳር 11 /2017 ዓ.ም
ጂንካ
የኢትዮጵያ የፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ እና ከፍተኛ ባለሙያዎች ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የኣሪ ዞን በጂንካ ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ማኔጅመንት አካላት ጋር የጋራ ውይይት አካሄዷል።
የውይይቱ ዓላማ በፀረ አበረታች ቅመሞች ዙሪያ የሚያጠነጥን ሲሆን በቀጣይ በተቀናጀ መልኩ እንዴት መስራት እንዳለባቸው የሚያመላክት ነው ።
ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ በውይይቱ በመድረኩ ያነሱ ሃሳብ በአበረታች ቅመሞች በአሁን ጊዜ በአስከፊ ሁኔታ ላይ በመሆኑና መከላከሉ ላይ ያለው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ በጋራ በመወያየት ዶፒንግን የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራዎቻችንን ተጠናክሮ መስራት እንደሚገባ ገልፀው ክልሉም በባለቤትነት ኃላፊነት ወስደው መንቀሳቀስ እንደሚገባ ተናግሯል።
ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የወጣቶች ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ እና አስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጅፋሬ እንዳሉት ዶፒንግ ለመከላከል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት መስራት እንደሚያስፈልግ እና መስተካከል ያለባቸው ጉዳዩች እያስተካከልን በባለቤትነት እንሰራለን በክልላችን ለሚሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ የተሳካ እንዲሆን ሙሉ ኃላፊነት እንወስዳለን በማለት ውይይቱ አጠናቋል ።





