የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የ9ኝ ወራት የእቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄደ፡፡
ሚያዝያ 4/2017 ዓ.ም
አዳማ
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው በ2017 በጀት ዓመት በ9 ወር ውስጥ ባከናወኗቸው ተግባራት ላይ የባለስልጣኑ አመራሮች እና አጠቃላይ ሰራተኞች በተገኙበት ውይይትና ግምገማ ተካሄዷል ፡፡
የውይይት መድረኩን የመሩት የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል እንደተናገሩት በማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ መሰራት የሚገባቸው ሥራዎች ተለቅሞ መሰራት አለባቸው በጀት አመቱ እየጨረሰን እየሄድን ነው የታቀዱ ሥራዎች ሳይፈፀም ቀረ የምንለው ለይተን በዛ ደረጃ ማጠናከር ይኖርብናል ብለዋል።
ተቋማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል አፈፃፀማችንንም እያደገ መጥቷል ግን አሁንም ተወዳዳሪ መሆን አለብን ተወዳዳሪነታችንን እየጠገን መሄድ አለብን ወደ ተሻለ ደረጃ ምዕራፍ ማሸጋገር ያስፈልጋል ስለዚህ ተቋማችን ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲቀጥል ውጤታማ ሆኖ እንዲቀጥል በአለም አቀፍ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በአግባብ መገንዘብ እና የምንሰራቸው ሥራዎች በአለም አቀፍ ዕይታና መመዘኛ መስፈርት መሠረት ውጤታማ ናቸው አይደሉም በሚለው እያዩ መሄድ ያስፈልጋል ስለዚህ የኛ ተቋም አፈፃፀም በየጊዜው እያደገ መሄድ መቻል አለበት በማለት አቶ መኮንን ገልፀዋል።
አክለውም ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቋማት እያደረጉ ናቸው የመንግሥት ተቋማት አብዛኞቹ ራሳቸውን ሪፎርም አርገው ተወዳዳሪነቱ በጣም እያደገ መጥቷል ስለዚህ እኛም በዛ ደረጃ ራሳችንን እያሳደግን ተቋማችን ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል ።
የቡድን ሥራ መጠናከር አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀው የሥራ ክፍል ሀላፊዎች ባለሞያዎ በቡድን መሥራት ባህል እንደሆነ እንዲያስቡ ማድረግና በተናጥል የሚሰሩ ሥራዎች ብዙ ውጤት አያመጡም በተናጥል የሚሰሩ ሥራዎች ተደምረው ነው ውጤት የሚያመጡት ስለዚህ ለመደመር ዝግጁ መሆን አለብን የቡድን ሥራ የአንድ ተቋም ተልዕኮ ለማሳካት አስፈላጊ ነው ለኛ ተቋም ደግሞ ዋናው መርሃችን በቡድን ነው ስራን የምንሰራው ቡድናዊ ስሜት በተቋሙ መፍጠር ይኖርብናል ብለዋል።
በመጨረሻም ዴይሬክተሩ እንደተናገሩት የስራ ባህላችን እንደ ሀገር በጣም ዝቅተኛ ነው መስተካከል አለበት እንደ ተቋማችን ውስጥ ያለነው ባለሙያ የሥራ ባህላችን ማሳደግ ያስፈልገናል ለግላችንም እንዲሁ ለተቋሙ የሚጠቅም ነው የስራ ባህላችን ማሳደግ ያስፈልጋ በማለት መልዕክት አስተላልፏል።
የተቋሙ የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወር የሥራ አፈጻጻም ዝርዝር ሪፖርት በወ/ሮ ስርጉት በየነ በስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አማካኝነት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል ፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *