የፀረ-አበረታች ቅመሞች የህግ ጥሰት በፈፀሙ አትሌቶች ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈባቸው።
አትሌት ህብስት ጥላሁን አስረስ፤ አትሌት ሳሙኤል አባተ ዘለቀ እና አትሌት ፀሐይ ገመቹ በያን የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግ በመጠቀም የህግ ጥሰት የፈፀሙ መሆኑ ተረጋግጧል።
በዚህም መሠረት አትሌት ፀሐይ ገመቹ በያን በተደረገላት የአትሌት ባይሎጂካል ፖስፖርት (ABP) ምርመራ አበረታች ቅመም መጠቀሟ የተረጋገጠ ሲሆን እ.ኤ.አ ከNovember 30/2024 ጀምሮ ለ4 ዓመታት በማንኛውም የስፖርት ውድድር እንዳትሳተፍ እና ከ2020 እስከ November 30/2024 ጀምሮ ያስመዘገበችው ውጤት እንዲሰረዝ ቅጣት ተጥሎባታል።
እንዲሁም አትሌት ህብስት ጥላሁን አስረስ ቻይና ሀገር ውስጥ በነበረው ውድድር ላይ በተካሄደው ምርመራ Triamcinolone acetonide የተባለውን የተከለከለ ንጥረ ነገር መጠቀሟ የተረጋገጠ ሲሆን እ.ኤ.አ ከJune 3/2024 ጀምሮ ለ2 ዓመታት በማንኛውም የስፖርት ውድድር እንዳትሳተፍ እገዳ ተጥሎባታል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ አትሌት ሳሙኤል አባተ ዘለቀ እ.ኤ.አ February 29/2023 በተካሄደው ምርመራ EPO (Erythropoietin) የተባለውን የተከለከለ ንጥረ ነገር መጠቀሙ በመረጋገጡ እ.ኤ.አ ከApril 17/2024 ጀምሮ ለ2 ዓመታት በማንኛውም የስፖርት ውድድር እንዳይሳተፍ እገዳ ተጥሎበታል፡፡
በቀጣይም በሀገራችን በየደረጃው የሚደረገው ምርመራና ቁጥጥር ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የስፖርት አበረታች ቅመሞችን በመጠቀምም ይሁን በተለያዩ መልኩ የፀረ-ዶፒንግ የህግ ጥሰት በሚፈፅሙ አትሌቶችና ከጀርባ ሆነው በሚተባበሩ ሌሎችም ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን የእርምት እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ይገልፃል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *