የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ለለገጣፎና ለገዳዲ ከተማ አሰተዳደር ስር ለሚገኙ አትሌቶች እና ለስፖርት ባለሞያዎች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
’’ በአሥራ ሰባት የስልጠና አይነቶች የፀረ-ዶፒንግን ጉዳይ በማስልጠኛ ማኑዋል ውስጥ ተካቶ ስልጠና ለመስጠት በትኩረት የሰራ መሆኑን፣ በአጭር ግዜ ውስጥም ወደተግባር እደሚሸጋገር ’’ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ገለፀ ፡፡
ሥልጠናው በኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን፣በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ወጣቶችና ስፖርት ቢሮና እና በከተማ አስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የተዘጋጀ ሲሆን ለአትሌቶች እና ለስፖርት ባለሞዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጥታል፡፡
በሥልጠናው ላይ በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ ለክለብ አትሌቶች፣ ለታዳጊ ፕረጀከት አትሌቶች እዲሁም ለስፖርት ባለሞዎችና ለድጋፍሰጪ ሠራተኞች በስፖርት አበረታች ቅመሞች መሰረታዊ ጉዳዮች፣ በሚያስከትለው ጉዳት፣በዶፒንግ ህግ ጥሰትና በተያያዥ ዙሪያ ግንዛቤ እዲያኙ የተዘጋጀ ሲሆን፡፡
በተጨማሪም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ስፖርትና ወጣቶች ቢሮ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በጋራ መከላከልና መቆጣጠር በሚቻልበት መንገድ ላይ እያደረገ ስላለው እንቅስቃሴ ገለፃ ተደርጓል፡፡
በበጀት ዓመቱ የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በአሥራ ሰባት የስልጠና አይነቶች ውስጥ የፀረ-ዶፒንግን ጉዳይ በማስልጠኛ ማኑዋል ውስጥ አካቶ ስልጠና ለመስጠት በትኩረት እየሰራ መሆኑን፣ በአጭር ግዜ ውስጥም ወደተግባር እደሚገባ’’ የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የውድድርና ስልጠና ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መኮንን በቀለ ጠቁመዋል፡፡
በሌላ በኩል በተለይ የህግ ጥሰቶቹ በአብዛኛው የሚፈፀሙትና ስፖርተኞች በብዛት በሚገኙባቸው በ5 የፊንፊኔ ልዩ ዞን (በሱሉልታ፣ በሰበታ፣ ቡራዩ፣ ገላንና ለገጣፎ) አካባቢዎች ላይ ኮሚቴ ተቋቅሞ የኢንተለጀንስና ኢንቨስቲጌሽን ስራ እየተሰራ ስለመሆኑም አቶ መኮንን በቀለ ጨምረው ገልፀዋል ፡፡
በመድረኩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየው ሲሳይ ፤ አሰልጣኝ ኮማነደር ሁሴን ሽቦ የስፖርቱ አመራሮችና ባለሞያዎች ጨምሮ በስልጠናው መድረክ ላይ ከ 65 በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ስልጠናው የሰጡት የባለስልጣኑ የትምርት፣ስልጠና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፈለቀ ዋለልኝ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የስጋት አካባቢያቸውን በመለየት ችግር በአግባቡ በመከታተል በዘላቂነት ለመቅረፍ ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስፖርት ኮሚሽን እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመሆን የኢንተለጀንስና ኢንቨስቲጌሽን ስራውን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማካሄድ እና ውጤታማነቱንም ለማጎልበት የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽንን ጨምሮ የሶስትዮሽ የፓርትነርሽፕ ፕሮግራም ለመዘርጋት የሚያስችል የውል ስምምነት ሰነድ ተፈረራርሞ ወደ ተግባር እንዲሸጋገር መደረጉን ከባለስልጣኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *