ለመቻል እና ለይጋጨፌ ቡና ሴቶች እግርኳስ ክለብ ስልጠና ተሰጠ ፡፡
ሐዋሳ ከተማ፡ ህዳር 15 ቀን 2015 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ለሴቶች ፕሪምር ሊግ እግር ኳስ ክለቦች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የሚሰጠው ስልጠና በዛሬው ዕለትም የቀጠለ ሲሆን በተለይም በቀጣይነት አትሌቶች ሊያውቋቸውና ተግባራዊ ሊያደርጓቸው በሚገቡ ጉዳየች ዙሪያ ሰፊ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ በስልጠናው መድረክ ላይ እደተናገሩት አትሌቶች ከስልጠናቸው ጎንለጎን ስለአበረታች ቅመሞች/ዶፒንግ ምንነቱን፣የአሰራር ስራዓቱን፣ ህጉን፣ ጉዳቱን ጠንቅቆ መገንዘብ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
የዚህ ስልጠና መድረክ ዋና ዓላማም ስፖርተኞው ስለስፖርት አበረታች ቅመሞች/ ዶፒንግ መሰረታዊ ጉዳየችን እና የአሰራር ስርዓቶችን አውቃችውና ተግንዝባችው ተግባራዊ በማድረግ እራሳችውን ከዶፒንግ እድትጠብቁ ለማስቻል መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የስፖርት ፌድሬሽኖች እና ክለቦች በፀረ-አበረታች ቅመሞች ዙሪያ ለአትሌቶቻቸው በየግዜው ግንዛቤ የመፍጠር፣የማስተማር ህጋዊም ግዴታ እዳለባቸው ም/ዋና ዳይሬክተሯ አስታውቀዋል፡፡
በዛሬው የፀረ-አበረታች ቅመሞች ወይም የፀረ-ዶፒንግ የስልጠና መድረክ ውሎ ላይ የመቻል እና የይጋጨፌ ቡና ሴቶች እግርኳስ ክለብ አትሌቶችና የአትሌት ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ተሳታፊ ሁነዋል ፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *