ለስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር ባለሞያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በመካሄድ ላይ ይገኛል ።
መስከረም 27/2015 ዓ/ም
በኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን /ETH-ADA/ አዘጋጅነት ለስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር ባለሙያዎች በዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር እና አጠቃላይ እንቅስቃሴ ዙሪያ በአዳማ ከተማ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው ፡፡
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ በፕሮግራሙ መክፈቻ ወቅት እንደተናገሩት ተቋማችን ውጤታማ የሆኑ ስራዎችን እንዲሰራ በብዙ ፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ በመሆን በበጎ ፈቃደኝነት አገራችሁን እና ህዝባችሁ በቅንነት ማገልገል በመቻላችሁ በተቋማችን ስም እናመሰግናለን ብለዋል፡፡
አያይዘውም የዚህ የስልጠና ዋነኛ ዓላማ በስራ ሂደታችን ወቅት የሚያስፈልጉን ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮች በመፈተሽ የነበሩ ክፍተቶች የምናይበትና ጥንካሬዎቻችንን በማስቀጠል ለቀጣይ ስራዎቻችን ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እንድንችል ታስቦ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ እንደሆነ በንግግራቸው ጠቁመዋል፡፡
በመድረኩ 40 የሚሆኑ የዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር የበጎ ፍቃድ ባለሙያዎች /Chaperones,DCOs and BCOs/ተሳትፈዋል ።
ስልጠናው ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን የበጉ ፈቃደኝነት እንቅስቃሴ በተቋማችን ምን ይመስላል፣ በ2014 ዓ/ም የነበረው የስራ አፈጻጸም እና የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችስ ፣ በ2022/23 የምርመራ ናሙና መሰብሰቢያ ኪቶችን በሚመለከት እንዲሁም የምርመራ ባለሙያዎች የስራ ደረጃ እድገትና በስራ ውል ስምምነት ዙሪያ በተለያዩ ባለሙያዎች የንድፈ ሐሳብ ገለፃ (Theoretical) እና የተግባር ልምምድን (Practice) የሚያካትት ስልጠና የሚሰጥ ይሆናል።

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *