ለባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ሳይንስ ተማሪዎች ስልጠና ተሰጠ፡፡
ETH-NADO has provided Anti-Doping Training for Sport Science undergraduate students of Bihar Dar University.
The University Sport Academy would do its level best to provide the necessary support to the Office, the Research and Community Service vice Dean with the Sport Academy, Dr. Teketle Abraham said
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት (ETH-NADO) ግንቦት 23/213 ዓ.ም ለባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዋች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ፡፡
ስልጠናዉ በዩኒቨርሲቲዉ ስፖርት አካዳሚ አዳራሽ የተሰጠ ሲሆን፤ 30 የሚሆኑ የ2013 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
በስልጠናዉ መክፈቻ ላይ የተገኙት በዩኒቨርሲቲዉ የስፖርት አካዳሚ የሪሰርችና ኮሚኒቲ ስረቪስ ምክትል ዲን የሆኑት ዶ/ር ተከተል አብርሀም በስልጠናዉ መክፈቻ ላይ ተገኝተዉ ባደረጉት ንግግር ዶፒንግ በአሁኑ ወቅት በስፖርቱ እንቅስቃሴ ላይ የተከሰተ ወረርሽኝ እደሆነ ገልጸው፤ በቀጣይ የስፖርት አካዳሚዉ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ጋር በስልጠና፣በጥናትና ምርምርእና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ፍላጎት እዳለዉ ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም ለተዘጋጀዉ ስልጠና ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በስልጠናዉ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬ ክተር ክቡርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ ጽ/ቤታቸዉ ዶፒንግ ለመከለከልና ለመቆጣተር የተደረገ ስላለዉ አጠቃላይ እንቅስቃሴ እና በዶፒንግ  ዓለማቀፋዊ ገፅታ ላይ ገለፃ አድርገዋል፤ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በስልጠናው የዶፒንግ ታሪካዊ አመጣጣና ምንንነት ፣ የአሰራር ስርዓቶች በተመለከተ የጽ/ቤቱ የትምህርት፤ ስልጠናና የጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ፈለቀ ዋለልኝ የተሰጠ ሲሆን፤ የዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር ሂደትን በተመለከተ በአቶ ዳንኤል ተስፋዬ የፀረ-ዶፒንግ የስልጠና ከፍተኛ ባለሞያ ተሰጥቷል ፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *