ለቦንጋ ዮኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ ተመሪቂ ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ተካሄደ።
ሚያዝያ 08/2014 ዓ.ም
ቦንጋ ከተማ
“የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ የንፁህ ስፖርት የውድድር መርህ በማዛባት በአቋራጭ ለመክበር የሚደረግ የማጭበርበር ተግባር የሆነ በዜጎች ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያሰከትል አደገኛ የስፓርት ውድድር ወረርሽኝ ነው። “
ይህ የተገለፀው የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመምች ባለሥልጣን /ETH ADA / ሚያዝያ 09 ቀን 2014 ዓ.ም ለቦንጋ ዮኒቨርሲቲ ስፖርት ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ምክትል አከደሚክ ዲን አቶ አበራ ኃይሌ አዲሎ በመድረኩ ተገኝተው ባሰተላለፉት መልዕክት ነው።

By Ermias