ለጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት ማስልጠኛ ማዕከል አመራሮች፤አሰልጣኞችና ለህክምና ባለሞያዎች በዶፒንግ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

Anti-Doping Awareness Creation Training being offered to Some 20 Tirunshe Dibaba’s Sport Training Centre Administrator, Coaches, and Health professionals

(ETH-NADO ህዳር 30/2013 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ከ20 ለሚበልጡ ለጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት ማስለጠኛ ማዕከል አመራሮች፤አሰልጣኞችና ለህክምና ባለሞያዎች በአሰላ ከተማ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ላይ ትምህርት ተሰጠ፡፡

በሥልጠናውን ፕሮግራም ላይ ተግኝተው ንግግር ያደረጉት የጽ/ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ እደተናገሩት በአገራችን ዶፒንግን ለመከላከልና ለመቆጣጣር የስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላት ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ጽ/ቤቱ የተለያዩ የስልጠና እና የጋራ ውይይት መድረኮችን በማዘጋጀትየስፖርተኞችን፤የስፖርት ባለሞያዎችንና አመራሮች ግነዛቤ የማሳደግ ስራ እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫው ዋና ዓላማ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን የሚመለከቱ ጉዳዮች በማስልጠኛ ማዕከላት ካሪኩለም ውስጥ እንዲካተትና ተግባራዊ እንዲሆን ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን፤ በቀጣይ የክትትልና ድጋፍ ስራ እንደ ሚሰራም ም/ ዋና ዳይሬክተሯ አያይዘው ግልጸዋል፡፡

በቀረበው የስልጠና ማኑዋለል ላይ ከተሳታፊው ለተነሳው ጥያቄዎች በም/ዋና ዳይሬክተሯ ማብራሪያ ተስጥቷል፡፡
ሥልጠናው በነገው ዕለት የሚቀጥል ሲሆን፤ለማዕከሉ አትሌቶችና ለአስታዳደር ባለሞያዎች ስልጠና ይሰጣል፡፡
Image may contain: 1 person, standing

Image may contain: 1 person, sitting, shoes and indoor

Image may contain: 1 person, indoorImage may contain: 1 person, sitting and indoor

Image may contain: one or more people, people standing and shoes

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *