ሚያዚያ 09/20🙄14 ዓ.ም
ቴፒ ከተማ
የኢትዮጵያ የፀረ አበረታች ጥቅሞች ባለስልጣን / ETH ADA /በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ለማጎልበት በመሰራት ላይ መሆኑን አሰታወቀ።
በስልጠናው ወቅት የሚዛን ቴፒ ዮኒቨርሲቲ የቴፒ ካንፓስ ኃላፊ አቶ ይገረም ማሞ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ዶፒንግ በስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ጉዳት የማያስከትል ፤የዜጎችን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል ፤የአገርን መልካም ገፅታ የሚያበላሽ ተግባር ነው።ሁላችንም በጋራ ልንሰራ ይገባል በማለት ተናግረው ተሳታፊዎች በትኩረት እዲከታተሉ አሳስበዎል።
የኢትዮጵያ ፀረ- አበረታች ጥቅሞች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ዶፒንግን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እየተደረገ ሰላለው እንቅስቃሴ ገልፁው፤ የስፖርት ሳይንስ ባለሙያው የዶፒንግን ምንነቱን፣ህጉን፣ አሰራሩንና ጉዳቱን ተገንዝባችው ሌሎችን የማስወቅ፤ የማስገንዘብ ሙያዊ ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልፀዎል።
ስልጠናው ትኩረት ያደረገበት ነጥብ የዶፒንግ መሠረታዊ ፅንሰ ሃሳቦች፤ የአሰራር ስርአቶች በህግ ማዕቅፍች፣ በጤና ጉዳቶቹና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የተመለከቱ ናቸው።
በመጨረሻም የተፈጥሮ ሳይንስ ና የከፕቴሽን ሳይንስ ኮሌጅ ዲን እደተናገሩት ባለስልጣኑ እረዝም ጎዞ ተጉዞ ይህንን መድረክ አዘጋጅቶ ግንዛቤ መፍጠሩ እንዳስደሰታቸው የተሰጡት ገለፃዎችም ግንዛቤአቸውን እዳሰፋላቸው ጠቁመው ባለስልጣን መስሪያቤቱ ላደረገው አስተዎፅ ምስጋና አቅርበዎል።

By Ermias