ሰልጣኞች ከስፖርት ስልጠና ጎን ለጎን ስለዶፒንግ ምንነት፤በተዘረጉ አሰራር ሥርዓቶች ዙሪያ ዕውቀት ሊኖራቸዉ እደሚገባ ተገለፀ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/ETH-NADO/ የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ለሚያሰለጥናቸዉ ሰልጣኖች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ጉዳዮች እና በተዘረጉ የአሰራር ሥርአቶች ላይ ከግንቦት 27-28/2013 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የተሰጠዉ ስልጠና ተጠናቋዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ክብር አቶ መኮነን ይደርሳል በስልጠናዉ ማጠቃለያ ንግግራቸው፤‹‹የህይወት ጥሪያችዉን ስፖረት ላይ ላደረጋችዉ ታዳጊ ስፖርተኞች ፤በዶፒንግ ምንነት፤በተዘረጉ ያሰራር ስርአቶች ዙሪያ በቂ የሆነ ዕውቀት፣ግንዛቤ ሊኖራችዉ ፤ይገባል፡፡››ብለዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በአህጉር አቀፍ ሆነ በአለም ዓቀፍ ሻምፒዮናዎች ተሳታፊ ለመሆን፤የተሳትፎ መወዳደሪያ መስፈርቶችን ማሟላት በቻ በቂ ነበር፤ ባለንበት ዘመን ግን የዶፒንግ አጀንዳ ዋነኛ መስፈርት ሆኗል፡፡
ከወጣትነት ጋር ተያይዞ የሚመጡ መሰናክሎችን ተቋቅማችዉ የአገራችሁን ስም ማስጠራት ይጠበቅባችዋል፤‹‹ታዳጊ ስፖርተኞች የህይዎት ጥሪያችዉ ስፖርት ስለሆነ››፤ ከዚህ ግባችዉ ሊያወጣችዉ ከሚችለዉ ዶፒንግ እራሳቸዉን መጠበቅ አለባችሁ ፤በአትሌቲክስ ዘረፍ ኢትዮጵያ ዝና አላት ይህ ስምና ዘናዋን ልታስቀጥሉ የምትችሉት እናንተ ናችዉ በማለት ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘዉ ገልፀዋለ፡፡
አስከትለዉም፤በመጀመሪያ ደረጃ በግልም ሆነ፣በቡድን ስፖርት ጠንካራ ስነ-ልቦና መገንባት ያስፈልጋል፤ የእናተን ተተኪነት ሊያረጋግጡ የሚችለዉ የተሟላ ክህሎት፣ዕዉቀት፤ስነ- ምግባር፣ የስነ-ልቦና ዝግጁነታችዉ የተሟላ ሲሆን ነዉ ፡፡ተወዳድሮ ማሻነፍ እችላለው የሚል የህይዎት ክህሎት ማዳበር አለባችዉ፤ብለዋል፡፡
‹‹እደ ጽ/ቤታቸዉ ከስፖርት አካዳሚዉ ጋር በጋራ ለዉጤት እድትበቁ አስፈላጊዉን ድጋፍ እናደርጋልን ፤ በቀጣይ በእናንተ ግዜ ዶፒንግ ይቆማል ብዬ አምናለዉ፤ በናንተ ወጣቶች መቀየር አለበት፡››በማለት ዋና ዳይሬክተሩ ተናግድረዋል፡፡
በመጨረሻ ዋና ዳይሬክተሩ ክብር አቶ መኮነን ይደረሳል፤‹‹የተሰጣችሁን ስልጠና በመልካም ዲሲፕሊን፤ በትኩረት ስለከታተላችዉ በጣም እንወዳችዋለን፤እናከብራችዋለን›› ብለዋል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *